ዘኍል 12:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ማርያምም ከሰፈሩ ውጪ ሰባት ቀን ተዘግቶባት ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተገለለች፤ ከዚያ እስክትመለስም ሕዝቡ ጕዞውን አልቀጠለም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያም በኋላ ማርያም ከሰፈር ወጥታ ለብቻዋ ተዘግቶባት ቈየች፤ እርስዋ እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ ከሰፈር አልተንቀሳቀሱም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ማርያምም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተለይታ ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትነጻ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማርያምም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተዘግታ ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም። |
የነጻውም ሰው ልብሱን ያጥባል፥ ጠጉሩንም ሁሉ ይላጫል፥ በውኃም ይታጠባል፥ ንጹሕም ይሆናል፤ ከዚያም በኋላ ወደ ሰፈር ይገባል፥ ነገር ግን ከድንኳኑ በውጭ ሆኖ ሰባት ቀን ይቀመጣል።
ጌታ ሆይ፥ ዝናህን ሰምቻለሁ፥ በሥራህም ጌታ ሆይ ፈራሁ፥ በዓመታት መካከል አድሰው፥ በዓመታት መካከል አስታውቀው፥ በቁጣ ጊዜ ምሕረትን አስብ።