Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘኍል 12:15 - አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ከዚያም በኋላ ማርያም ከሰፈር ወጥታ ለብቻዋ ተዘግቶባት ቈየች፤ እርስዋ እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ ከሰፈር አልተንቀሳቀሱም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ስለዚህም ማርያም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተገለለች፤ ከዚያ እስክትመለስም ሕዝቡ ጕዞውን አልቀጠለም ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ማርያምም ከሰፈሩ ውጪ ሰባት ቀን ተዘግቶባት ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ማር​ያ​ምም ከሰ​ፈር ውጭ ሰባት ቀን ተለ​ይታ ተቀ​መ​ጠች፤ ማር​ያ​ምም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ሕዝቡ አል​ተ​ጓ​ዙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ማርያምም ከሰፈር ውጭ ሰባት ቀን ተዘግታ ተቀመጠች፤ ማርያምም እስክትመለስ ድረስ ሕዝቡ አልተጓዙም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘኍል 12:15
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አባትህንና እናትህን አክብር፤ ይህን ብታደርግ እኔ በምሰጥህ ምድር የረዥም ዘመን ዕድሜ ይኖርሃል።


ምንም እንኳ ጭንቀት በሰው ላይ እንዲደርስ ቢፈቅድ ከተትረፈረፈ ዘለዓለማዊ ፍቅሩ የተነሣ ይራራል።


ከበሽታው የነጻው ሰው ልብሱን ያጥባል፤ ጠጒሩን ሁሉ ይላጫል፤ ሰውነቱንም ይታጠባል፤ ከዚያም በኋላ የነጻ ሆኖ ወደ ሰፈር ይገባል፤ ነገር ግን እስከ ሰባት ቀን ከራሱ ድንኳን ውጪ መቈየት አለበት።


ከግብጽ አወጣሁህ፤ ከባርነት ምድርም ታደግኹህ፤ ሙሴን፥ አሮንንና ማርያምን በፊትህ መሪዎች አድርጌ ሰጠሁህ።


እግዚአብሔር ሆይ! ስላደረግኸው አስደናቂ ሥራ ሁሉ ሰምቼ እጅግ ፈራሁ፤ አሁንም በዘመናችን የቀድሞውን ሥራህን ደግመህ አድርግ፤ በየዘመናቱም እንዲታወቅ አድርግ፤ በምትቈጣበት ጊዜ እንኳ ምሕረትህን አታርቅ።


ከዚያም በኋላ ከሐጼሮት ተነሥተው በፋራን ምድረ በዳ ሰፈሩ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች