ማቴዎስ 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ሰዎች መጾማቸውን እንዲያዩላቸው ፊታቸውን ይለውጣሉና፤ እውነት እላችኋለሁ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ስትጾሙ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ እነርሱ መጾማቸው እንዲታወቅላቸው ሆነ ብለው በፊታቸው ላይ የሐዘን ምልክት ያሳያሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ እንዲህ የሚያደርጉ ዋጋቸውን በሙሉ ተቀብለዋል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኢየሱስም ቀጥሎ እንዲህ አለ፦ “በምትጾሙበት ጊዜ፥ መጾማቸውን ሰዎች እንዲያውቁላቸው፥ ፊታቸውን እንደሚለውጡት እንደ ግብዞች፥ ፊታችሁን አታጠውልጉ፤ በእውነት እላችኋለሁ፥ እነርሱ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስትጦሙም፥ እንደ ግብዞች አትጠውልጉ፤ ለሰዎች እንደ ጦመኛ ሊታዩ ፊታቸውን ያጠፋሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል። |
አገልጋዮቹም፥ “እንደዚህ ያደረግኸው ለምንድን ነው? ሕፃኑ በሕይወት እያለ ጾምህ፤ አለቀስህ፤ ሕፃኑ ከሞተ በኋላ ግን ተነሥተህ በላህ” ብለው ጠየቁት።
የእስራኤልም ልጆች ተሰለፉ፥ ሊገጥሙአቸውም ወጡ፥ የእስራኤልም ልጆች እንደ ሁለት ትናንሾች የፍየል መንጋዎች ሆነው በፊታቸው ሰፈሩ፥ ሶርያውያን ግን ምድሩን ሞልተው ነበር።
እናንተም እንዲህ ብላችኋል፦ እግዚአብሔርን ማገልገል ከንቱ ነው፤ ትእዛዙን መጠበቅ፥ በሠራዊት ጌታ ፊት ኀዘንተኞች ሆነን መሄድ ምን ይጠቅመናል?
“ሰዎች እንዲያዩላችሁ ብላችሁ መልካምም ሥራችሁን በፊታቸው እንዳታደርጉ ተጠንቀቁ፤ አለበለዚያ በሰማያት ካለው አባታችሁ ዘንድ ሽልማት አታገኙም።
“እንግዲህ ምጽዋት ስታደርግ፥ ግብዞች በሰዎች ዘንድ እንዲከበሩ በምኵራቦችና በመንገድ እንደሚያደርጉት በፊትህ መለከት አታስነፋ፤ እውነት እላችኋለሁ፥ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
“ስትጸልዩ እንደ ግብዞች አትሁኑ፤ በሰዎች ለመታየት ሲሉ በየምኵራቡ ና በየመንገዱ ማዕዘን ቆመው መጸለይን ይወዳሉና፤ እውነት እላችኋለሁ፤ ዋጋቸውን ተቀብለዋል።
የዮሐንስ ደቀ መዛሙርትና ፈሪሳውያን ይጾሙ ነበር። መጥተውም “የዮሐንስና የፈሪሳውያን ደቀ መዛሙርት የሚጾሙት የአንተ ደቀ መዛሙርት ግን የማይጾሙት ስለ ምንድነው?” አሉት።
ቆርኔሌዎስም እንዲህ አለው “በዚች ሰዓት የዛሬ አራት ቀን የዘጠኝ ሰዓት ጸሎት በቤቴ እጸልይ ነበር፤ እነሆም፥ የሚያንጸባርቅ ልብስ የለበሰ ሰው በፊቴ ቆመና
ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።