Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ነህምያ 1:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እነዚህን ቃላት በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ። ለብዙ ቀኖች አዘንሁ፤ በሰማይ አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ይህን ነገር በሰማሁ ጊዜ አያሌ ቀናት ዐዘንሁ፤ ጾምሁ፤ በሰማይ አምላክም ፊት ጸለይሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እኔም ይህን ሁሉ በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስኩ። ለብዙ ቀኖችም በጾምና በሐዘን ቈየሁ፤ ወደ እግዚአብሔርም እንዲህ ስል ጸለይኩ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ይህ​ንም ቃል በሰ​ማሁ ጊዜ ተቀ​ምጬ አለ​ቀ​ስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰ​ማ​ይም አም​ላክ ፊት እጾ​ምና እጸ​ልይ ነበር፤ እን​ዲ​ህም አልሁ፦

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ይህንም ቃል በሰማሁ ጊዜ ተቀምጬ አለቀስሁ፤ አያሌ ቀንም አዝን ነበር፤ በሰማይም አምላክ ፊት እጾምና እጸልይ ነበር፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ነህምያ 1:4
22 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በባቢሎን ወንዞች አጠገብ በዚያ ተቀመጥን፥ ጽዮንንም ባሰብናት ጊዜ አለቀስን።


ዕዝራ በእግዚአብሔር ቤት ፊት በግንባሩ ወድቆ እያለቀሰ በሚጸልይበትና በሚናዘዝበት ጊዜ፤ ወንዶች፥ ሴቶችና ሕፃናት የሚገኙበት እጅግ ታላቅ ጉባኤ ወደ እርሱ ተሰበሰበ፥ ሕዝቡም እጅግ አለቀሱ።


ንጉሡም፦ “ምን ትፈልጋልህ?” አለኝ። እኔም ወደ ሰማይ አምላክ ጸለይሁ።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።


ከበዓሉ ርቀው የሚያዝኑትን፥ ከአንቺም የሆኑትን እሰበስባለሁ፤ ስድብ እንደ ሸክም ከብዶባቸው ነበር።


ይህንንም ነገር በሰማሁ ጊዜ ልብሴንና ካባዬን ቀደድሁ፥ የራሴን ጠጉርና ጢሜንም ነጨሁ፥ ደንግጬም ተቀመጥሁ።


እርሱም፦ “እኔ ዕብራዊ ነኝ፥ ባሕሩንና የብሱን የፈጠረውን፥ የሰማይን አምላክ እግዚአብሔርን አመልካለሁ” አላቸው።


ዳዊት ስለ ሕፃኑ እግዚአብሔርን ለመነ፤ ጾመም፤ ወደ ክፍሉ ገብቶም ሌሊቱን መሬት ላይ ተኝቶ ዐደረ።


የሰማይን አምላክ አመስግኑ፥ ፍቅሩ ለዘለዓለም ነውና።


ይህችን ቦታና ሕዝብዋን የተረገሙና ባድማ እንደማደርግ የተናገርኩትን ቃል በሰማህ ጊዜ ልብህ ተነክቶ ራስህን በማዋረድ፥ ልብስህን በመቅደድና በፊቴም በማልቀስህ ጸሎትህን ሰምቼአለሁ።


ሰሎሞንም ርዝመቱ አምስት ክንድ፥ ወርዱም አምስት ክንድ፥ ቁመቱም ሦስት ክንድ የሆነ የናስ መደገፊያ ሠርቶ በአደባባዩ መካከል ተክሎት ነበር፥ በእርሱም ላይ ቆመ፥ በእስራኤልም ጉባኤ ሁሉ ፊት በጉልበቱ ተንበርክኮ እጁን ወደ ሰማይ ዘርግቶ፥


የፋርስ ንጉሥ ቂሮስ እንዲህ ይላል፦ “የሰማያት አምላክ ጌታ የምድርን መንግሥታት ሁሉ ሰጥቶኛል፥ በይሁዳም ባለችው በኢየሩሳሌም ቤት እንድሠራለት አዝዞኛል፤


በሠርክ መሥዋዕት ጊዜ ልብሴና ካባዬ እንደተቀደደ ከተዋረድኩበት ተነሣሁ፥ በጉልበቴም ተንበርክኬ ወደ ጌታ አምላኬ እጄን ዘረጋሁ፤


እኔም፦ “የሰማይ አምላክ ያከናውንልናል፥ እኛም አገልጋዮቹ እንነሳለን፥ እንሠራለንም፤ እናንተ ግን በኢየሩሳሌም ድርሻ ወይም መብት ወይም መታሰቢያ የላችሁም” ብዬ መለስኩላቸው።


አገልጋዮችህ ድንጋዮችዋን ወድደዋልና፥ ለመሬትዋም አዝነዋልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች