24 ጉልበቶቼ በጾም ደከሙ፥ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
24 ከጾም የተነሣ ጕልበቴ ዛለ፤ ሰውነቴም ከስቶ ዐመድ ለበሰ።
24 ጒልበቶቼ በጾም ደከሙ፤ ሥጋዬም ቅቤ በማጣት ከሳ።
ስለዚህ የላሉትን እጆቻችሁን የሰለሉትንም ጉልበቶቻችሁን አቅኑ።
አርባ ቀንና አርባ ሌሊት ከጾመ በኋላ ተራበ።
እንደ ነጣቂና እንደሚያገሣ አንበሳ በላዬ አፋቸውን ከፈቱ።
በድካምና በጥረት፥ በእንቅልፍ አልባ ሌሊቶች፥ በራብና በጥም፥ ብዙ ጊዜም በመራብ፥ በብርድና በመታረዝ አሳልፌለሁ።
የቤትህ ቅንዓት በልታኛለችና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በላዬ ወድቆአልና።
አጥንቴ ከቁርበቴና ከሥጋዬ ጋር ተጣበቀ፥ ድድ ብቻ ቀርቶልኝ አመለጥሁ።
ነፍሴን በጾም አስመረርሁአት፥ ለስድብም ሆነብኝ።