Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 11:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 በድካምና በጥረት፥ በእንቅልፍ አልባ ሌሊቶች፥ በራብና በጥም፥ ብዙ ጊዜም በመራብ፥ በብርድና በመታረዝ አሳልፌለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ብዙ ጥሬአለሁ፤ ብዙ ደክሜአለሁ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ ተርቤአለሁ፤ ተጠምቻለሁ፤ ብዙ ጊዜ ምግብ ሳልቀምስ ኖሬአለሁ፤ በብርድና በዕራቍትነት ተቈራምጃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ብዙ ሥራና ድካም ነበረብኝ፤ ብዙ ጊዜ እንቅልፍ አጥቻለሁ፤ በራብና በውሃ ጥም ተጨንቄአለሁ፤ ብዙ ጊዜም የምግብ እጦት ደርሶብኛል፤ ብርድና መራቆትም ደርሶብኛል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 በድ​ካ​ምና በጥ​ረት፥ ብዙ ጊዜም ዕን​ቅ​ልፍ በማ​ጣት፥ በመ​ራ​ብና በመ​ጠ​ማት፥ አብ​ዝ​ቶም በመ​ጾም፥ በብ​ር​ድና በመ​ራ​ቆት ተቸ​ገ​ርሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 በድካምና በጥረት ብዙ ጊዜም እንቅልፍ በማጣት፥ በራብና በጥም ብዙ ጊዜም በመጦም፥ በብርድና በራቁትነት ነበርሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 11:27
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጥቂትም ማግኘትን አውቃለሁ፤ ብዙም ማግኘትን አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ የመጥገብንና የመራብን ብዙ የማግኘትንና የማጣትን ምሥጢር ተምሬአለሁ።


በመገረፍ፥ በመታሰር፥ በሁከት፥ በድካም፥ እንቅልፍ በማጣት፥ በመራብ፥


ወንድሞች ሆይ! ድካማችንንና ጥረታችንን ታስታውሱታላችሁ፤ የእግዚአብሔርን ወንጌል ለእናንተ እየሰበክን በአንዳችሁም ላይ እንኳ ሸክም ላለመሆን ስንል ሌሊትና ቀን እንሠራ ነበር።


ከእናንተ ዘንድ በማንም ላይ ሸክም እንዳንሆንበት ሌሊትና ቀን በድካምና በጥረት እየሠራን እንኖር ነበር እንጂ የማንንም ሰው እንጀራ እንዲያው በነፃ አልበላንም።


በድንጋይ ተወግረው ሞቱ፤ በመጋዝ ተሰነጠቁ፤ በሰይፍ ተገድለው ሞቱ፤ ሁሉን እያጡ መከራን እየተቀበሉ፥ እየተጨነቁ፥ የበግና የፍየል ሌጦ ለብሰው ዞሩ።


እንደ እብድ ሰው እናገራለሁ፤ እኔ እበልጣቸዋለሁ፤ በሥራ ብዙ ደክሜአለሁ፥ ብዙ ጊዜ ታስሬለሁ፥ ብዙ ግርፋት ደርሶብኛል፥ ብዙ ጊዜ እስከ መሞት ደርሻለሁ።


ለጸሎት ለመትጋት ተስማምታችሁ ለተወሰነ ጊዜ ካልሆነ በቀር፥ እርስ በርሳችሁ አትከላከሉ፤ እንዲሁም ራሳችሁን ስለ አለመግዛት ሰይጣን እንዳይፈታተናችሁ አብራችሁ ሁኑ።


በየቤተ ክርስቲያኑም ሽማግሌዎችን ከሾሙላቸው በኋላ ጦመውም ከጸለዩ በኋላ፥ ላመኑበት ለጌታ አደራ ሰጡአቸው።


“ጌታዬ ንጉሥ ሆይ! እነዚህ ሰዎች ነቢዩን ኤርምያስን በጉድጓድ ውስጥ ጥለው ባደረጉበት ነገር ሁሉ ክፉ ነገርን ፈጽመዋል፤ በከተማይቱም ውስጥ እንጀራ ስለ ሌለ በዚያ በራብ ይሞታል።”


ስለዚህ ሦስት ዓመት ሌሊትና ቀን በእንባ እያንዳንዳችሁን ከመገሠጽ እንዳላቋረጥሁ እያሰባችሁ ትጉ።


እንዲህ ዓይነቱ በጸሎትና በጾም ካልሆነ በቀር ከቶ አይወጣም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች