ሉቃስ 11:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው። ዐይንህ ጤናማ በሆነ ጊዜ ሰውነትህ ሁሉ ደግሞ በብርሃን የተመላ ይሆናል። ዐይንህ ታማሚ በሆነ ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ በጨለማ የተመላ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ናት፤ ዐይንህ ጤናማ ስትሆን መላ ሰውነትህ ብሩህ ይሆናል፤ ዐይንህ ታማሚ ከሆነች ግን መላ ሰውነትህ የጨለመ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው፤ ዐይንህ ጤናማ ከሆነ ሰውነትህ ሁሉ በብርሃን የተሞላ ይሆናል፤ ዐይንህ ግን ታማሚ ከሆነ መላ ሰውነትህ ሁሉ ጨለማ ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የሰውነትህ መብራት ዐይንህ ነው፤ ዐይንህ ብሩህ ከሆነ ሰውነትህ ሁሉ ብሩህ ነው፤ ዐይንህ ታማሚ ቢሆን ግን፤ ሰውነትህ ሁሉ ጨለማ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የሰውነትህ መብራት ዓይንህ ናት። ዓይንህ ጤናማ በሆነች ጊዜ ሰውነትህ ሁሉ ደግሞ ብሩህ ይሆናል። ዓይንህ ታማሚ በሆነች ጊዜ ግን ሰውነትህ ደግሞ የጨለመ ይሆናል። |
ከአገልጋዬ በቀር ዕውር ማን ነው? እንደምልከው መልእክተኛዬስ ደንቆሮ የሆነ ማን ነው? እንደ ፍጹም ተገዢዬ ወይም እንደ ጌታ አገልጋይ ዕውር የሆነ ማን ነው?
ክፉውን መልካም፤ መልካሙን ክፉ ለሚሉ ብርሃኑን ጨለማ፤ ጨለማውን ብርሃን ለሚያደርጉ፤ ጣፋጩን መራራ፤ መራራውንም ጣፋጭ ለሚያደርጉ ወዮላቸው!
የዚህን ሕዝብ ልብ አደንድን፤ ጆሮአቸውን ድፈን፤ ዐይኖቻቸውንም ክደን፤ ይህ ካልሆነማ፤ በዐይናቸው አይተው፤ በጆሮአቸው ሰምተው፤ በልባቸውም አስተውለው በመመለስ ይፈወሳሉ።”
አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።
ትምክህታችን ይህ ነው፦ በዚህ ዓለም ይልቁንም በእናንተ ዘንድ፥ በእግዚአብሔር ጸጋ እንጂ በሥጋዊ ጥበብ ባልሆነ፥ በእግዚአብሔር ቅድስናና ቅንነት እንደኖርን፥ የሕሊናችን ምስክርነት ነው።
እንደ እነርሱ ከሆነ የማያምኑ ሰዎችን ልቦና፥ የእግዚአብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፥ የዚህ ዓለም አምላክ አሳውሯል።
ባርያዎች ሆይ! ሰውን ደስ ለማሰኘት ስትሉ ለታይታ የምትገዙ አትሁኑ፤ ነገር ግን በቅን ልብ ጌታን እየፈራችሁ ለምድራዊ ጌቶቻችሁ በሁሉ ታዘዙ።