ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።
ኤርምያስ 9:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “እያንዳንዱ ወንድም አታላይ፣ ባልንጀራም ሁሉ ሐሜተኛ ስለ ሆነ፣ ወንድም ከወንድሙ ይጠንቀቅ፤ ባልንጀራም በጓደኛው አይታመን። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እያንዳንዱ ከባልንጀራው ተንኰል ይጠንቀቅ፤ ወንድሙን እንኳ ቢሆን ማመን የለበትም፤ ወንድም የተባለ ሁሉ (እንደ ያዕቆብ) አታላይ ሆኖአል፤ ወዳጅ የተባለም ሁሉ የባልንጀራውን ስም ያጠፋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ በጠማማነት ይሄዳልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፤ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ። |
ሰውየውም፦ “ከእንግዲህ ወዲህ ስምህ ያዕቆብ አይባልም፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ከሰውም ጋር ታግለህ አሸንፈሃልና እስራኤል ይባላል” አለው።
ስለዚህ ጌታ በጎበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።
የሁላችን አባት አንድ አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማርከስ ሁላችንም ለምን ወንድማችንን እናታልላለን?
አስቀድመን ደግሞ እንደ ነገርናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና፥ ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ፤ ወንድሙንም አያታልል።