Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገሩም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ባልንጀራ ባልንጀራውን ያታልላል፤ እውነትን የሚናገር የለም፤ ሐሰትን ይናገሩ ዘንድ ምላሳቸውን አሠልጥነዋል፤ ኀጢአትንም በማድረግ ራሳቸውን አድክመዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ሁሉም ባልንጀራውን በማሞኘት ያሳስታል፤ እውነት የሚናገርም የለም፤ አንደበታቸው ውሸት መናገርን እንዲለማመድ አድርገውታል፤ ኃጢአት በመሥራት ሰውነታቸውን ያደክማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 እያ​ን​ዳ​ንዱ በባ​ል​ን​ጀ​ራው ላይ ይሣ​ለ​ቃል በእ​ው​ነ​ትም አይ​ና​ገ​ርም፤ ሐሰት መና​ገ​ር​ንም ምላ​ሳ​ቸው ተም​ሮ​አል፤ በደሉ መመ​ለ​ስ​ንም እንቢ አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገርም፥ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 9:5
32 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እነሆ፥ አሕዛብ ለእሳት እንደሚሠሩ፥ ሕዝቦችም ለከንቱነት እንደሚደክሙ ከሠራዊት ጌታ ዘንድ የሆነ አይደለምን?


ባለ ጠጎችዋ ግፍ ተሞልተዋል፤ በውስጧ የሚኖሩትም ሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው።


በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፤ የጉልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም።


በደልህ ንግግርህን ይመራዋል፥ የተንኰለኞችንም አንደበት ትመርጣለህ።


ይህም ትምህርት ኅሊናቸውን በጋለ ብረት በማቃጠል አደንዝዘው ውሸትን በሚናገሩ ግብዞች በኩል የሚሰጥ ነው፤


ስለዚህ ውሸትን አስወግዳችሁ፥ እርስ በርሳችን የሰውነት አካሎች ሆነናልና እያንዳንዳችሁ ከባልንጀሮቻችሁ ጋር እውነትን ተነጋገሩ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ምን አደረግሁህ? ያደከምኩህስ እንዴት ነው? መልስልኝ።


ብዙ ለፍታ ደከመች፥ ሆኖም የዝገቱ ክምር በእሳት እንኳ አልለቀቀም።


ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ፤ ሰው ከባልንጀራው ጋር በሰላም ይናገራል፥ በልቡ ግን ያደባበታል።


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


ኃጢአትን በማታለል ገመድ ለሚስቡ፤ በደልንም በሠረገላ ማሰሪያ ለሚጐትቱ ወዮላቸው!


ክፉ ካላደረጉ አይተኙምና፥ ካላሰናከሉም እንቅልፋቸው ይወገዳልና።


በልባቸውም ክፉ ካሰቡ፥ ቀኑን ሁሉ ለሰልፍ ከሚከማቹ።


ከክፉዎች ደባ፥ ከዓመፀኞችም ብዛት ሰውረኝ።


አፍህ ክፋትን አበዛ፥ አንደበትህም ሽንገላን ተበተበ።


የሞት መሣርያንም አሰናድቷል፥ ፍላጻዎቹንም የሚንበለበሉ አደረገ።


ከንቱ ልፍለፋህ ሰዎችን ዝም ያሰኛቸዋልን? ብትሳለቅስ የሚያሳፍርህ የለምን?


በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፥ ሰዎቹም ደጃፉን ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ።


ኃያል ሆይ፥ በክፋት ለምን ትኩራራለህ? ሁልጊዜስ በመተላለፍ?


አንተም፦ “የአምላኩን የጌታን ድምፅ ያልሰማ፥ ተግሣጽንም ያልተቀበለ ሕዝብ ይህ ነው፤ እውነት ጠፍቶአል ከአፋቸውም ታጥቶአል።


ወንድሞችህና የአባትህ ቤት እነርሱ ጭምር አታልለውሃልና፥ በኋላህም ጮኸዋልና፤ በመልካምም ቢናገሩህም አትመናቸው።”


ስንዴን ዘሩ እሾህንም አጨዱ፤ እራሳቸውን አደከሙ፥ ምንም አልረባቸውም፤ ስለ ጌታ ጽኑ ቁጣ በፍሬያችሁ ታፍራላችሁ።”


በውኑ ኢትዮጵያዊ መልኩን ወይስ ነብር ዝንጉርጉርነቱን መለወጥ ይችላልን? እናንተ ክፋትን የለመዳችሁ ደግሞ በጎ ለማድረግ ትችላላችሁ።


“የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ ሰፋፊዎቹ የባቢሎን ቅጥሮች ፈጽመው ይፈርሳሉ ረጃጅሞችም በሮችዋ በእሳት ይቃጠላሉ፤ ሕዝቡም በከንቱ ጉልበቱን ይፈስሳል፥ አሕዛብም የደከሙበት ነገር ለእሳት ይሆናል።”


አንተም እንዲህ በል፦ ‘እኔ ከማመጣባት ክፉ ነገር የተነሣ እንዲሁ ባቢሎን ትሰጥማለች አትነሣምም።’ ” የኤርምያስ ቃላት እስከዚህ ድረስ ነው።


የሁላችን አባት አንድ አይደለምን? የፈጠረንስ አንድ አምላክ አይደለምን? የአባቶቻችንን ቃል ኪዳን ለማርከስ ሁላችንም ለምን ወንድማችንን እናታልላለን?


ያ ሁሉ ትውልድ ወደ አባቶቹ ከተከማቸ በኋላ ጌታንም ሆነ እርሱ ለእስራኤል ሕዝብ ያደረገውን ነገር የማያውቅ ሌላ ትውልድ ተነሣ።


የጻድቃን አሳብ ቅን ነው፥ የክፉዎች ምክር ግን ሽንገላ ነው።


“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች