Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 9:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፤ ሽንገላን ይናገራሉ፤ ሰው ከባልንጀራው ጋር በሰላም ይናገራል፥ በልቡ ግን ያደባበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ምላሳቸው የሚገድል ቀስት ነው፤ በሽንገላ ይናገራል፤ ሁሉም ከባልንጀራው ጋራ በሰላም ይናገራል፤ በልቡ ግን ያደባበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 አንደበታቸው ዘወትር ተንኰል ስለሚናገር፥ እንደ አደገኛ ፍላጻ ነው፤ እያንዳንዱ ባልንጀራውን በፍቅር ቃል ያነጋግረዋል፤ ነገር ግን በስውር ወጥመድ ይዘረጋበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ምላ​ሳ​ቸው የተ​ሳለ ፍላጻ ነው፤ ንግ​ግ​ራ​ቸው ሽን​ገላ ነው፤ ለባ​ል​ን​ጀ​ራ​ቸው ሰላ​ምን ይና​ገ​ራሉ፤ በል​ባ​ቸው ግን ጥላ​ቻን ይይ​ዛሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ምላሳቸው የተሳለ ፍላጻ ነው፥ ሽንገላን ይናገራሉ ሰው ከባልንጀራው ጋር በሰላም ይናገራል፥ በልቡ ግን ያደባበታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 9:8
21 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከኃጥኣንና ከክፉ አድራጊዎች ጋር ነፍሴን አትውሰዳት፥ ክፋትም በልባቸው እያለ ከባልንጀራቸው ጋር ሰላም ከሚናገሩት ጋር አትጣለኝ።


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


ስለ ሽንገላ አንደበት ምንን ይሰጡሃል? ምንስ ይጨምሩልሃል?


ከሰማይ ልኮ አዳነኝ፥ ለረገጡኝም ውርደትን ሰጣቸው፥ እግዚአብሔር ቸርነቱንና እውነቱን ላከ።


ወዳጄ ከእርሱ ጋር ሰላም በነበሩት ላይ እጁን ዘረጋ፥ ኪዳኑንም አፈረሰ።


አቤቱ፥ አድነኝ፥ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።


አበኔርም ወደ ኬብሮን በተመለሰ ጊዜ፥ ኢዮአብ ለብቻው የሚያነጋግረው በመምሰል ወደ ቅጽሩ በር ይዞት ሄደ፤ እዚያም የወንድሙን የአሣሄልን ደም ለመበቀል ሆዱ ላይ ወግቶ ገደለው።


ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገሩም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።


በሕዝቤ መካከል ክፉዎች ሰዎች ተገኝተዋል፤ እንደ ወፍ አጥማጆችም ያደባሉ፥ ወጥመድንም ይዘረጋሉ ሰዎችንም ያጠምዳሉ።


እግዚአብሔርም ከፍ ከፍ ይላል። ድንገተኛ ፍላጻም ያቈስላቸዋል፥


በእርጋታ በምድሪቱ ለተቀመጡት ሰላምን አይናገሩምና፥ በቁጣም ሽንገላን ይመክራሉ።


በባልንጀራው ላይ በሐሰት የሚመሰክር እንደ መዶሻና እንደ ሰይፍ እንደ ተሳለም ቀስት ነው።


ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።


ባለ ጠጎችዋ ግፍ ተሞልተዋል፤ በውስጧ የሚኖሩትም ሐሰት ተናግረዋል፥ ምላሳቸውም በአፋቸው ውስጥ አታላይ ነው።


እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፥ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።


ከከፍታ ያናውጡት ዘንድ መከሩ፥ ሐሰትንም ይወድዳሉ፥ በአፋቸው ይባርካሉ፥ በልባቸውም ይረግማሉ።


በውኑ ስለ እነዚህ ነገሮች አልቀሥፍምን? ይላል ጌታ፤ ነፍሴስ እንደዚህ ባለ ሕዝብ ላይ አትበቀልምን?


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች