Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢሳይያስ 9:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ስለዚህ ጌታ በጎበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ይህን ሕዝብ የሚመሩት ያስቱታል፤ የሚመራውም ሕዝብ ከመንገድ ወጥቶ ይባዝናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይህን ሕዝብ የሚመሩት ሁሉ አሳስተውታል፤ ሕዝቡም ከመንገድ ወጥቶ ባዝኖአል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ይህን ሕዝብ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግኑ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤ ይበ​ሉ​አ​ቸ​ውም ዘንድ ያስ​ቱ​አ​ቸ​ዋል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ይህን ሕዝብ የሚመሩ ያስቱአቸዋል፥ ተመሪዎቹም ይጠፋሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢሳይያስ 9:16
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ካህናቱና ሌዋውያኑም ተነሥተው ሕዝቡን ባረኩ፤ ድምጻቸውም ተሰማ፥ ጸሎታቸውም ወደ ቅዱስ መኖሪያው ወደ ሰማይ ዐረገ።


ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


ጌታ ግራ የመጋባት መንፈስ በውስጥዋ አፍሶባታል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት።


ወጣቶች ሕዝቤን ያስጨንቃሉ፤ ሴቶችም ይገዟቸዋል። ሕዝቤ ሆይ፤ መሪዎችህ አሳስተውሃል፤ ከመንገድህም መልሰውሃል።


የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ስለዚህ ልጆቻቸውን ለራብ ስጥ፥ ለሰይፍም እጅ አሳልፈህ ስጣቸው፥ ሚስቶቻቸውም የወላድ መካንና መበለቶች ይሁኑ፥ ወንዶቻቸውም በሞት ይጥፉ፥ ጉልማሶቻቸውም በጦርነት ጊዜ በሰይፍ ይመቱ።


በሰማርያ ነቢያት መካከል አጸያፊን ነገር አይቻለሁ፤ በበዓል ትንቢት ይናገሩ ነበር፥ ሕዝቤንም እስራኤልን ያስቱ ነበር።


ወንድምም ሁሉ ያሰናክላልና፥ ባልንጀራም ሁሉ ያማልና እናንተ ሁሉ ከባልንጀሮቻችሁ ተጠንቀቁ፥ በወንድሞቻችሁም አትታመኑ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “የጌታን ሕግ ጥለዋልና፥ ትእዛዙንም አልጠበቁምና፥ አባቶቻቸውም የተከተሉአቸው ሐሰቶቻቸው አስተዋቸዋልና ስለ ሦስት የይሁዳ ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ጌታ ሕዝቤን ስለሚያስቱ ነቢያት እንዲህ ይላል፦ ሰው ሲያበላቸው “ሰላም አለ” ይላሉ፤ ካላበላቸው ግን ጦርነት ሊያውጁበት ይነሣሉ።


ተዉአቸው፤ ዕውሮችን የሚመሩ ዕውሮች ናቸው፤ ዕውር ዕውርን ቢመራ ሁለቱም ወደ ጉድጓድ ይወድቃሉ።”


ታናሹ በታላቁ እንደሚባረክ ምንም ጥርጥር የሌለውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች