ኤርምያስ 5:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህ ሕዝብ ግን እልኸኛና ዐመፀኛ ልብ አለው፤ ዐምፀዋል ሄደዋልም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሕዝብ ግን የሸፈተና እልኸኛ ልብ አለው፤ መንገድ ለቅቆ ሄዷል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ ግን እልኸኛና ዐመፀኛ ሕዝብ በመሆናችሁ፥ እኔን ትታችሁ ኰብልላችኋል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዚህም ሕዝብ የማይሰማና የዐመፀ ልብ አላቸው፤ ተመልሰውም ሄደዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለዚህ ሕዝብ ግን የሸፈተና ያመፀ ልብ አላቸው፥ ዐምፀዋል ሄደውማል። |
ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እነርሱንም አናግራቸዋለሁ፤ የጌታን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና” አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።
እኔ ዓመፃችሁንና የአንገታችሁን ድንዳኔ አውቃለሁና፥ እኔም ዛሬ ከእናንተ ጋር ገና በሕይወት ሳለሁ እናንተ በጌታ ላይ ዐምፃችኋል፥ ይልቁንስ ከሞትሁ በኋላ እንዴት ይሆናል?