Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 21:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 “አንድ ሰው፥ የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፥ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 አንድ ሰው፣ የአባቱን ወይም የእናቱን ትእዛዝ የማይሰማ፣ ቢቀጡትም የማይታረም እልከኛና ዐመፀኛ ልጅ ቢኖረው፣

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 “አንድ ሰው ምንም ቢቀጡት የማይመለስ እልኸኛና ዐመፀኛ ሆኖ፥ ለወላጆቹ የማይታዘዝ ልጅ ይኖረው ይሆናል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “ማንም ሰው ለአ​ባቱ ቃልና ለእ​ናቱ ቃል የማ​ይ​ታ​ዘዝ፥ ቢገ​ሥ​ጹ​ትም የማ​ይ​ሰ​ማ​ቸው ትዕ​ቢ​ተ​ኛና ዐመ​ፀኛ ልጅ ቢኖ​ረው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ማንም ሰው ለአባቱ ቃልና ለእናቱ ቃል የማይታዘዝ ቢቀጡትም የማይሰማቸው እልከኛና ዓመፀኛ ልጅ ቢኖረው፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 21:18
31 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ከእናንተ እያንዳንዱ ሰው እናቱንና አባቱን ያክብር፥ ሰንበታቴንም ጠብቁ፥ እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝ።


“ጌታ አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም፥ አባትህንና እናትህን አክብር።


ለምን ዳግመኛ ትመታላችሁ? ለምንስ በዐመፅ ትጸናላችሁ? ራሳችሁ በሙሉ ታሞአል፤ ልባችሁ ሁሉ ታውኮአል።


ሰማያት ሆይ፤ ስሙ! ምድር ሆይ፤ አድምጪ! ጌታ እንዲህ ተናግሮአልና፤ “ልጆች ወለድሁ፤ አሳደግኋቸውም፤ እነርሱ ግን ዐመጹብኝ።


በአባትዋ የምታላግጥን የእናትዋንም ትእዛዝ የምትንቅን ዐይን የሸለቆ ቁራዎች ይጐጠጉጡአታል፥ አሞራዎችም ይበሉአታል።


ልጅህን ቅጣ ዕረፍትንም ይሰጥሃል፥ ለነፍስህም ደስታን ይሰጣታል።


አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፥ በጽቅድቅ ጨለማ መብራቱ ይጠፋል።


ተስፋ ገና ሳለች ልጅህን ገሥጽ፥ መሞቱንም አትሻ።


በርኩሰትሽ ሴሰኝነት አለ፥ መዓቴን በአንቺ ላይ እስክጨርስ ድረስ ከእንግዲህ ወዲያ ከርኩሰትሽ ንፁህ አትሆኚም ምክንያቱም አነጻሁሽ ነገር ግን ንፁህ አልሆንሺምና።


አባትንና እናትን አቃለሉ፥ በመካከልሽ መጻተኛውን ጨቆኑ፥ በአንቺ ውስጥ የሙት ልጅንና መበለቲቱን አስጨነቁ።


በእውነት ኤፍሬም ሲያለቅስ ሰማሁ፦ ‘ቀጣኸኝ እኔም እንዳልተገራ ወይፈን ተቀጣሁ፤ አንተ ጌታ አምላኬ ነህና መልሰኝ እኔም እመለሳለሁ።


አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።


አባቱን የሚረግም፥ እናቱንም የማያመሰግን ትውልድ አለ።


ከአባቱና ከእናቱ እየሰረቀ፦ “አላጠፋሁም” የሚል የአጥፊ ሰው ባልንጀራ ነው።


ቂልነት በልጅ ልብ ውስጥ ተተብትቧል፥ የተግሣጽ በትር ግን ነፃ ያደርገዋል።


ሰነፍ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚቀበል ግን አእምሮው የበዛ ነው።


በበትር ከመምታት የሚራራ ሰው ልጁን ይጠላል፥ ልጁን የሚወድድ ግን ተግቶ ይገሥጸዋል።


ልጄ ሆይ፥ የአባትህን ምክር ስማ፥ የእናትህንም ሕግ አትተው፥


አባት እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጄ ይሆናል። በደል በሚፈጽምበትም ጊዜ ሰዎች በሚቀጡበት በትር እቀጣዋለሁ፤ የሰው ልጆችም በዐለንጋ እንደሚገረፉ እገርፈዋለሁ።


“‘አባቱን ወይም እናቱን የሚያቃልል የተረገመ ይሁን!’ “ሕዝቡም ሁሉ፥ ‘አሜን!’ ይበል።


እንግዲህ ሰው ልጁን እንደሚገሥፅ፥ እንዲሁም ጌታ እግዚአብሔር አንተን እንደሚገሥጽህ በልብህ አስተውል።


የካህንም ልጅ ራስዋን በዝሙት ብታረክስ አባትዋን ታረክሰዋለች፤ በእሳት ትቃጠል።


አባቱን ወይም እናቱን የሚያዋርድ ፈጽሞ ይሙት።


አባቱን ወይም እናቱን የሚመታ ፈጽሞ ይሙት።


አባትና እናቱ ይዘው በሚኖሩበት ከተማ በር ወዳሉት አለቆች ያምጡት፤


ልጆቹ አስጸያፊ ነገር ሲያደርጉ እርሱ ባለመከልከሉ፥ ዔሊ በሚያውቀው ኃጢአት ምክንያት በቤተሰቡ ላይ ለዘለዓለም እንደምፈርድ ነግሬው ነበር።


ይህ ሕዝብ ግን እልኸኛና ዐመፀኛ ልብ አለው፤ ዐምፀዋል ሄደዋልም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች