Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኤርምያስ 5:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እነርሱንም አናግራቸዋለሁ፤ የጌታን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና” አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ስለዚህ ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ፤ ለእነርሱም እናገራለሁ፤ በርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድ፣ የአምላካቸውንም ሕግ ያውቃሉና።” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ ያው እንደዚያው ቀንበሩን ሰብረዋል፤ እስራቱንም በጥሰዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 እንግዲህ በሥልጣን ላይ ወዳሉት ገዢዎች ሄጄ፥ ከእነርሱ ጋር እነጋገራለሁ፤ በእርግጥ እነርሱ የእግዚአብሔርን መንገድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉ፤” ነገር ግን እነርሱም ቢሆኑ በእግዚአብሔር ላይ ዐምፀዋል፤ ለእርሱም መታዘዝ እምቢ ብለዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ወደ ታላ​ላ​ቆቹ እሄ​ዳ​ለሁ እና​ገ​ራ​ቸ​ው​ማ​ለሁ፤ እነ​ርሱ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገ​ድና የአ​ም​ላ​ካ​ቸ​ውን ፍርድ ያው​ቃ​ሉና።” እነ​ዚህ ግን ቀን​በ​ሩን በአ​ን​ድ​ነት ሰብ​ረ​ዋል፤ እስ​ራ​ቱ​ንም ቈር​ጠ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ወደ ታላላቆቹ እሄዳለሁ እናገራቸውማለሁ፥ የእግዚአብሔርን መንገንድና የአምላካቸውን ሕግ ያውቃሉና አልሁ። እነዚህ ግን ቀንበሩን በአንድነት ሰብረዋል፥ እስራቱንም ቈርጠዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኤርምያስ 5:5
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።


የአገሩ ሰዎች ግን ይጠሉት ነበርና ‘ይህ በላያችን እንዲነግሥ አንፈልግም፤’ ብለው በኋላው መልእክተኞችን ላኩ።


ኢየሱስም በዛም እንዳዘነ አይቶ “ሀብት ላላቸው ሰዎች ወደ እግዚአብሔር መንግሥት መግባት እንዴት ጭንቅ ይሆናል።


የካህን ከንፈሮች ዕውቀትን መጠበቅ አለባቸው፤ ሰዎችም ሕግን ከአፉ መፈለግ አለባቸው፤ ምክንያቱም የሠራዊት ጌታ መልእክተኛ ነው።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።


“እናንተ በሰማርያ ተራራ ያላችሁ፥ ድሆችንም የምትበድሉ፥ ችግረኛውንም የምትጨቁኑ፥ ጌቶቻቸውንም፦ ‘አምጡ እንጠጣ’ የምትሉ እናንተ የባሳን ላሞች ሆይ! ይህን ቃል ስሙ።


“ከታናናሾቻቸው ጀምሮ እስከ ታላላቆቻቸ ድረስ ሁሉም በግፍ ለሚገኝ ጥቅም ስስታም ናቸውና፥ ከነቢዩም ጀምሮ እስከ ካህኑ ድረስ ሁሉም ተንኰልን ይፈጽማሉ።


ሙሴ በጠላቶቻቸው ፊት መሳለቂያ እንዲሆኑ አሮን ስድ ለቅቋቸዋልና ሕዝቡ ስድ እንደ ተለቀቁ ባየ ጊዜ፥


ምላሳቸውን ስለ ሐሰት እንደ ቀስት ገተሩ፤ በምድር በረቱ ነገር ግን ለእውነት አይደለም፤ ከክፋት ወደ ክፋት ይሄዳሉና፥ እኔንም አላወቁምና፥ ይላል ጌታ።


እርሱም እንዲህ አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ እነዚህ ክፋትን የሚያቅዱና በዚህችም ከተማ ክፉ ምክርን የሚመክሩ ሰዎች ናቸው።


ደግሞም የካህናቱ አለቆች ሁሉ ሕዝቡም እንደ አሕዛብ ያለ ርኩሰት ሁሉ በመከተል መተላለፍን አበዙ፤ በኢየሩሳሌምም ጌታ ራሱ የቀደሰውን የጌታን ቤት አረከሱ።


ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።


ትውልድ ሆይ! የጌታን ቃል ተመልከቱ። በውኑ ለእስራኤል ምድረ በዳ ወይስ የጨለመች ምድር ሆንኩባትን? ሕዝቤስ ስለምን፦ ‘እኛ ፈርጥጠናል፤ ዳግመኛ ወደ አንተ አንመጣም’ ይላሉ?


እንዲሁም ሽመላ በሰማይ ጊዜዋን አውቃለች፤ ዋኖስና ጨረባ ዋልያም የመምጫቸውን ጊዜ ይጠብቃሉ፤ ሕዝቤ ግን የጌታን ፍርድ አላወቁም።


ውሽሞችህ ሁሉ ረስተውሃል አይፈልጉህምም፤ በደልህ ታላቅ ስለሆነ ኃጢአትህም ስለ በዛ፥ ጨካኝ ሰው እንደሚቀጣው ጠላትም እንደሚያቆስለው አቁስዬሃለሁና።


በጽዮን ላሉ ዓለመኞች፥ በሰማርያም ተራራ ላይ ተማምነው ለተቀመጡ፥ የእስራኤልም ቤት ወደ እነርሱ ለመጡባቸው ለአሕዛብ አለቆች ወዮላቸው!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች