ያዕቆብ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ምላስም እንደ እሳት ናት፤ በሰውነት ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ የክፋት ዓለም ናት፤ ሰውነትን ሁሉ ታረክሳለች፤ ደግሞም የፍጥረትን ሩጫ ታቃጥላለች፤ ራሷም በገሃነም ትቃጠላለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ምላስም እንደ እሳት ናት፤ ምላስ በአካል ክፍሎቻችን መካከል የምትገኝ ክፉ ዓለም ናት፤ አካላችንን ትበክላለች፤ ከገሃነም እንደሚወጣ እሳትም የኑሮአችንን ሂደት ሁሉ ታቃጥላለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በሰውነታችን ክፍሎች መካከል ዐመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፤ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፤ በገሃነምም ይቃጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንደበትም እሳት ነው። አንደበት በብልቶቻችን መካከል ዓመፀኛ ዓለም ሆኖአል፤ ሥጋን ሁሉ ያሳድፋልና፥ የፍጥረትንም ሩጫ ያቃጥላል፥ በገሃነምም ይቃጠላል። |
የይሁዳም ሰዎች ሁሉ፥ ለእስራኤል ሰዎች፥ “ይህን ያደረግነው ንጉሡ የቅርብ ዘመዳችን ስለሆነ ነው፤ ታዲያ ይህ እናንተን የሚያስቆጣ ነገር ነው? እኛ ከንጉሡ ተቀብለን አንዳች በልተናልን? ለራሳችንስ ምን የወሰድነው ነገር አለ?” አሉአቸው።
እነሆ፥ እሳት የምታነድዱ፥ የእሳትንም ወላፈን የምትታጠቁ ሁላችሁ፥ በእሳታችሁ ነበልባል ባነደዳችሁትም ወላፈን ሂዱ! ይህ ከእጄ ይሆንባችኋል፤ በኅዘን ትተኛላችሁ።
የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።
የእስራኤላዊቱም ልጅ የጌታን ስም ሰደበ፥ አቃለለውም፤ ወደ ሙሴም አመጡት። እናቱም ከዳን ነገድ የደብራይ ልጅ ነበረች፥ ስምዋም ሰሎሚት ነበረ።
እነሆ፥ እነዚህ በፌጎር ምክንያት በበለዓም ምክር ጌታን አታልለው ለእስራኤል ልጆች ዕንቅፋት ሆኑ፤ በዚህም ምክንያት በጌታ ማኅበር ላይ መቅሠፍት ሆነ።
እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወንድሙን የሚቆጣ ሁሉ ፍርድ ይገባዋል፤ ወንድሙን ‘የማያስብ’ የሚለው ሁሉ የሸንጎ ፍርድ ይገባዋል፤ ‘ደደብ’ የሚለውም ሁሉ የገሃነመ እሳት ፍርድ ይገባዋል።
እርሱም እየጮኸ ‘አብርሃም አባት ሆይ! ማረኝ፤ በዚህ ነበልባል እሠቃያለሁና የጣቱን ጫፍ በውሃ ነክሮ ምላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ላክልኝ፤’ አለ።
“የአባትህ፥ ወይም የእናትህ ልጅ ወንድምህ፥ ወንድ ልጅህ፥ ወይም ሴት ልጅህ ወይም የምትወዳት ሚስትህ ወይም የቅርብ ወዳጅህ አንዳቸው ቢሆኑ በምሥጢር ሊያስትህ ቢሞክር፥
ስለዚህ እኔ ከመጣሁ፥ ስለ እኛ የተናገረውን ክፉ ቃል፥ የሠራውን ሥራ አሳስበዋለሁ፤ ይህም ሳይበቃው እርሱ ራሱ ወንድሞችን አይቀበልም፤ ሊቀበሉአቸው የሚፈልጉትን ይከለክላቸዋል፥ ከቤተ ክርስቲያንም ያስወጣቸዋል።
ታላቁም ዘንዶ ወደ ታች ተጣለ፤ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።
በአውሬውም ፊት እንዲያደርግ ከተሰጡት ምልክቶች የተነሣ በምድር የሚኖሩትን ያስታል፤ የሰይፍም ቁስል ለነበረውና በሕይወት ለኖረው ለአውሬው ምስልን እንዲሠሩ በምድር የሚኖሩትን ያዛቸዋል።
የመብራትም ብርሃን ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይበራም፤ የሙሽራውና የሙሽራይቱም ድምጽ ከእንግዲህ ወዲህ በአንቺ ውስጥ ከቶ አይሰማም፤ ነጋዴዎችሽ የምድር መኳንንት ነበሩና፤ በአስማትሽም አሕዛብ ሁሉ ስተዋልና።”
አውሬውም ተያዘ፤ በእርሱም ፊት ተአምራትን እያደረገ የአውሬውን ምልክት የተቀበሉትን ለምስሉም የሰገዱትን ያሳተ ሐሰተኛውም ነቢይ ከእርሱ ጋር ተያዘ፤ ሁለቱም በሕይወት ሳሉ በዲን ወደሚቃጠል ወደ እሳት ባሕር ተጣሉ።