ኤርምያስ 28:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)16 ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘እነሆ፥ ከምድር ላይ አስወግድሃለሁ፤ በጌታ ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ’ ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘ከምድር ገጽ አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔርም ላይ ዐመፅ ተናግረሃልና፣ በዚህ ዓመት ትሞታለህ።’ ” ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም16 ስለዚህም እግዚአብሔር ‘አንተን ከምድረ ገጽ አስወግድሃለሁ ይህ ሕዝብ በእኔ በአምላካቸው ላይ እንዲያምፁ በማድረግህ ምክንያት ይህ ዓመት ከመፈጸሙ በፊት ትሞታለህ’ ይላል።” ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ ከገጸ ምድር አስወግድሃለሁ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዐመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ” አለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)16 ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ከምድር ላይ እሰድድሃለሁ፥ በእግዚአብሔር ላይ ዓመፅን ተናግረሃልና በዚህ ዓመት ትሞታለህ አለው። ምዕራፉን ተመልከት |