ዘፍጥረት 9:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የከነዓን አባት፥ ካምም፥ የአባቱን ዕራቁቱን መሆን አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የከነዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የከነዓን አባት የሆነው ካም፥ አባቱ ኖኅ እራቁቱን እንደ ሆነ ባየ ጊዜ ወደ ውጪ ወጥቶ፥ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው። |
ሴምና ያፌትም ልብስ በትከሻቸው ላይ አደረጉ፥ የኋሊትም ሄደው የአባታቸውን ዕራቁትነት አለበሱ፤ ፊታቸውም ወደ ኋላ ነበረ፥ የአባታቸውንም ዕራቁትነት አላዩም።
ወንድሞች ሆይ! ሰው ማንኛውንም ኃጢአት አድርጎ ቢገኝ፥ መንፈሳውያን የሆናችሁ እናንተ እንደዚህ ዓይነቱን ሰው በየውሃት መንፈስ አቅኑት፤ አንተም እንዳትፈተን ራስህን ጠብቅ።