Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 9:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 የከ​ነ​ዓን አባት ካምም የአ​ባ​ቱን ዕራ​ቁ​ት​ነት አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁ​ለቱ ወን​ድ​ሞቹ ነገ​ራ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 የከነዓን አባት ካም የአባቱን ዕርቃነ ሥጋ አየ፤ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 የከነዓን አባት፥ ካምም፥ የአባቱን ዕራቁቱን መሆን አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 የከነዓን አባት የሆነው ካም፥ አባቱ ኖኅ እራቁቱን እንደ ሆነ ባየ ጊዜ ወደ ውጪ ወጥቶ፥ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 የከነዓን አባት ካምም የአባቱን ዕራቁትነት አየ፥ ወደ ውጭም ወጥቶ ለሁለቱ ወንድሞቹ ነገራቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 9:22
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን የተ​ሳ​ሳተ ሰው ቢኖር በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የጸ​ና​ችሁ እና​ንት እን​ዳ​ት​ሳ​ሳቱ ለራ​ሳ​ችሁ እየ​ተ​ጠ​በ​ቃ​ችሁ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ​ውን ሰው ቅን​ነት ባለው ልቡና አጽ​ኑት።


ጽድ​ቅን በመ​ሥ​ራት ደስ ያሰ​ኛል እንጂ፥ ግፍን በመ​ሥ​ራት ደስ አያ​ሰ​ኝም።


“ወንድምህም ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ውቀሰው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ገንዘብ አደረግኸው፤


በጠ​ን​ካራ ቦታ ታድ​ነኝ ዘንድ አም​ላ​ኬና መድ​ኀ​ኒቴ ሁነኝ፤ ኀይ​ሌና መጠ​ጊ​ያዬ አንተ ነህና።


የካ​ምም ልጆች ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን ናቸው።


የካ​ምም ልጆች፤ ኩሽ፥ ምስ​ራ​ይም፥ ፉጥ፥ ከነ​ዓን።


ኖኅም እን​ዲህ አለ፥ “ከነ​ዓን ርጉም ይሁን፤ ለወ​ን​ድ​ሞ​ቹም የባ​ሪ​ያ​ዎች ባሪያ ይሁን።”


ሴምና ያፌ​ትም ልብስ ወስ​ደው በጫ​ን​ቃ​ቸው ላይ አደ​ረጉ፤ የኋ​ሊ​ትም ሄደው የአ​ባ​ታ​ቸ​ውን ዕራ​ቁ​ት​ነት አለ​በሱ፤ ፊታ​ቸ​ውም ወደ ኋላ ነበር፤ የአ​ባ​ታ​ቸ​ው​ንም ዕራ​ቁ​ት​ነት አላ​ዩም።


ኅፍረተ ሥጋውን ለማየት ባልንጀራውን ለሚያጠጣ፥ ክፉንም ለሚጨምርበት፥ ለሚያሰክረውም ወዮለት!


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች