Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ቆሮንቶስ 13:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 ፍቅር ከእውነት ጋራ እንጂ በዐመፅ ደስ አይሰኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ፍቅር ያለው ሰው እውነት በሆነ ነገር ይደሰታል እንጂ ትክክል ባልሆነ ነገር አይደሰትም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 ጽድ​ቅን በመ​ሥ​ራት ደስ ያሰ​ኛል እንጂ፥ ግፍን በመ​ሥ​ራት ደስ አያ​ሰ​ኝም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ቆሮንቶስ 13:6
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ክፉ በነፍሱ ፈቃድ ይኮራልና፥ ስግብግብም ይረግማል፥ ጌታንም ይንቃል።


ሕግህን አልጠበቅሁምና የውኃ ፈሳሽ ከዐይኖቼ ፈሰሰ።


ይትሮም ጌታ ለእስራኤል ስላደረገው መልካም ነገር ሁሉ፥ ከግብጽም እጅ ስላዳናቸው ደስ አለው።


ሰነፉ በኃጢአት ያፌዛል፥ በቅኖች መካከል ግን ቸርነት አለች።


ይህን ባትሰሙ ነፍሴ ስለ ትዕቢታችሁ በስውር ታለቅሳለች፤ የጌታም መንጋ ተማርኮአልና ዓይኔ እጅግ ታነባለች፥ እንባንም ታፈስሳለች።


የብዙ ሰዎችን የክፋት ሹክሹክታ ሰምቻለሁ፥ ማስፈራራትም ከብቦኛል። መውደቄን የሚጠብቁ የሰላሜ ሰዎች ሁሉ፦ “ምናልባት ይታለል እንደሆነ፥ እናሸንፈውም እንደሆነ፥ እርሱንም እንበቀል እንደሆነ፥ ክሰሱት እኛም እንከስሰዋለን” ይላሉ።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


የሕዝቤም ኃጢአት መብል ሆኖላቸዋል፥ ልባቸውንም ወደ በደላቸው አዘንብለዋል።


ንጉሡን በክፋታቸው፥ ሹማምንቱንም በሐሰታቸው ደስ ያሰኛሉ።


ጠላቴ ሆይ በእኔ ደስ አይበልሽ፤ ብወድቅ እነሣለሁና፤ በጨለማ ብቀመጥ ጌታ ብርሃኔ ነውና።


እውነት እላችኋለሁ፥ ባገኘው ጊዜ ካልጠፉት ከዘጠና ዘጠኙ ይልቅ በእርሱ ደስ ይለዋል።


እነርሱም ደስ አላቸው፤ ገንዘብም ሊሰጡት ተዋዋሉ።


“እነዚህን ነገሮች የሚያደርጉ ሞት ይገባቸዋል” የሚለውን ትክክለኛውን የእግዚአብሔርን ሕግ ቢያውቁም፥ እነዚህን ነገሮች ማድረግ ብቻ ሳይሆን፥ እንዲህ የሚያደርጉትንም ያበረታታሉ።


ፍቅር እውነተኛ ይሁን፤ ክፉውን ነገር ተጸየፉ፥ መልካም የሆነው ነገር አጥብቃችሁ ያዙ፤


ዳሩ ግን ይህ አድራጎታቸው ግድ የሚል ምን ነገር አለው? ብቻ በማመካኘትም ሆነ በእውነት በሁሉ መንገድ ክርስቶስ ይሰበክ እንጂ፤ ስለ ሆነም እኔ በዚህ ደስ ብሎኛል። ወደፊትም ደግሞ ደስ ይለኛል፤


ሁልጊዜ በጸሎቴ ሁሉ ስለ ሁላችሁም በደስታ እጸልያለሁ፤


ብዙዎች ለክርስቶስ መስቀል ጠላቶቹ ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ጊዜ ስለ እነርሱ ነገርኋችሁ፤ አሁንም እያነባሁ ስለ እነርሱ እነግራችኋለሁ።


በዚህም እውነቱን ያላመኑ ነገር ግን በዓመፅ ደስ የሚሰኙ ሁሉ ይፈረድባቸዋል።


ከልጆችሽ አንዳንዶቹ ከአባት እንደተቀበልነው ትእዛዝ መሠረት በእውነት የሚመላለሱ ሆነው በማግኘቴ እጅግ ደስ ብሎኛል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች