ዘፍጥረት 5:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ሔኖክ ማቱሳለን ወለደ፥ የእግዚአብሔርንም መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሔኖክ ማቱሳላን ከወለደ በኋላ አካሄዱን ከእግዚአብሔር ጋራ በማድረግ 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎች ወንዶችና ሴቶች ልጆችንም ወለደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ሔኖክ የእግዚአብሔርን መንገድ በመከተል 300 ዓመት ኖረ፤ ሌሎችንም ወንዶችና ሴቶች ልጆች ወለደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሄኖክም እግዚአብሔርን ደስ አሰኘው፤ ሄኖክም ማቱሳላን ከወለደ በኋላ ሁለት መቶ ዓመት ኖረ፤ ወንዶችንም፥ ሴቶችንም ወለደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ማቱሳላንም ከወለደ በኍላ የኖረው ሁለት መቶ ዓመት ሆነ ወለደ። |
እርሱም አለኝ፦ ‘አካሄዴን በፊቱ ያደረግሁለት እግዚአብሔር መልአኩን ከአንተ ጋር ይልካል፥ መንገድህንም ያቀናል፥ ለልጄም ከወገኖቼ ከአባቴም ቤት ሚስትን ትወስዳለህ፥
ያዕቆብም ዮሴፍን ባረከ እንዲህም አለ፦ “አባቶቼ አብርሃምና ይስሐቅ በፊቱ የሄዱለት እርሱ እግዚአብሔር፥ ከታናሽነቴ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ እኔን የመገበኝ እግዚአብሔር፥
በዚህ ሁሉ ነገር ታዛዥ ብትሆንለት፥ ‘ዘሮችህ በጥንቃቄ ተጠብቀው ቢኖሩ፥ በፍጹም ልባቸውና በፍጹም ነፍሳቸው በፊቴ በቅንነት ቢመላለሱ፥ በእስራኤል ዙፋን ላይ ነግሦ የሚገዛ ዘር አላሳጣህም’ ብሎ ጌታ የነገረኝን የተስፋ ቃል ይፈጽማል።
“እግዚአብሔር ሆይ! በታማኝነትና በቅንነት እንዳገለገልኩህ፥ አንተ የምትደሰትበትንም ነገር ለማድረግ ዘወትር እጥር እንደ ነበር ታስብ ዘንድ እለምንሃለሁ!” እያለ በመጸለይ ምርር ብሎ አለቀሰ።
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “እነሆ ከሰማይ እንጀራን ላዘንብላችሁ ነው፤ ሕዝቡም ወጥተው ለቀኑ የሚበቃቸውን በቀኑ ይልቀሙ በሕጌ ይሄዱ ወይም አይሄዱ እንደሆነ እፈትናቸዋለሁ።
ሳበኝ፥ ከአንተም በኋላ እንሮጣለን፥ ንጉሥ ወደ ቤቱ አገባኝ፥ በአንተ ደስ ይለናል፥ ሐሤትም እናደርጋለን፥ ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እናስባለን፥ በቅንነት ይወድዱሃል።
ኤፍሬም ሆይ! ከእንግዲህ ወዲህ ከጣዖታት ጋር እኔ ምን አደርጋለሁ? እኔ እመልስለታለሁ፥ ወደ እርሱም እመለከታለሁ፤ እኔ እንደ ለመለመ ጥድ ነኝ፤ ፍሬህ በእኔ ዘንድ ይገኛል።
ሰው ሆይ፥ መልካም ምን እንደሆነ ለአንተ ነግሮሃል፤ ፍትሕን እንድታደርግ፥ ምሕረትን እንድትወድና ከአምላክህም ጋር በትሕትና እንድትሄድ ካልሆነ በቀር ጌታ ከአንተ የሚፈልገው ምንድነው?
የእውነት ትምህርት በአፉ ውስጥ ነበረ፥ በከንፈሩም ውስጥ ስሕተት አልተገኘም፤ ከእኔ ጋር በሰላምና በቅንነት ሄደ፥ ብዙዎችንም ከኃጢአት መለሰ።
በይሁዳም ሁሉና በገሊላ በሰማርያም የነበሩት አብያተ ክርስቲያናት በሰላም ኖሩ፤ ታነጹም፤ በእግዚአብሔርም ፍርሃትና በመንፈስ ቅዱስ መጽናናት እየሄዱ ይበዙ ነበር።
የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።
በዚህም በበጎ ሥራ ሁሉ ፍሬ እያፈራችሁና በእግዚአብሔር እውቀት እያደጋችሁ፥ ለጌታ እንደሚገባው ፍጹም ደስ የሚያሰኘውን ሕይወት እንድትኖሩ ነው።
በመሆኑም ወደ መንግሥቱ ወደ ክብሩም ለጠራችሁ ለእግዚአብሔር እንደሚገባ እንድትመላለሱ እየመከርናችሁ፥ እያጸናናችሁና እየመሰከርንላችሁ ነበር።
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።
ነገር ግን እርሱ በብርሃን እንዳለ በብርሃን ብንመላለስ እርስ በእርሳችን ኅብረት አለን፥ የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል።