Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




2 ቆሮንቶስ 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖት ጋር ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፥ በእነርሱ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸውም እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖታት ጋራ ምን ስምምነት አለው? እኛ እኮ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን፤ እግዚአብሔርም እንዲህ ሲል ተናግሯል፤ “ከእነርሱ ጋራ እኖራለሁ፤ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፤ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ከጣዖቶች ጋር ምን ስምምነት አለው? እግዚአብሔርም፦ “መኖሪያዬን በሕዝቤ መካከል አደርጋለሁ፤ ከእነርሱም ጋር እኖራለሁ፤ እኔ አምላካቸው እሆናለሁ፤ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ” ብሎ እንደ ተናገረው እኛ እያንዳንዳችን የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦ​ትስ በጣ​ዖት ቤት ውስጥ የሚ​ያ​ኖር ማን ነው? የሕ​ያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ማደ​ሪ​ያ​ዎች እኛ አይ​ደ​ለ​ን​ምን? እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ሲል ተና​ገረ፥ “እኔ በእ​ነ​ርሱ አድ​ራ​ለሁ፤ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እኖ​ራ​ለሁ፤ አም​ላ​ካ​ቸ​ውም እሆ​ና​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ሕዝቤ ይሆ​ኑ​ኛል።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ለእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም ከጣዖት ጋር ምን መጋጠም አለው? እኛ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ነንና እንዲሁም እግዚአብሔር ተናገረ እንዲህ ሲል፦ በእነርሱ እኖራለሁ በመካከላቸውም እመላለሳለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ እነርሱም ሕዝቤ ይሆናሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




2 ቆሮንቶስ 6:16
60 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ታላቅም ድምፅ ከሰማይ ከዙፋኑ ወጥቶ እንዲህ ሲል ሰማሁ፦ “እነሆ የእግዚአብሔር ድንኳን በሰዎች መካከል ነው፤ ከእነርሱም ጋር ያድራል፤ እነርሱም ሕዝቡ ይሆናሉ፤ እግዚአብሔርም ራሱ ከእነርሱ ጋር ይሆናል፤ አምላካቸውም ይሆናል፤


በእስራኤል ልጆች መካከል አድራለሁ፥ አምላካቸውም እሆናለሁ።


ከዚያ ጊዜ በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የምገባው ቃል ኪዳን ይህ ነው፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፤ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆንላቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑልኛል።


በመካከላችሁም እመላለሳለሁ፥ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ፥ እናንተም ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ።


እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


ይህም በትእዛዜ እንዲሄዱ፥ ፍርዴንም እንዲጠብቁና እንዲፈጽሙ ነው፤ ስለዚህ እነርሱ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


ከእነዚያ ወራት በኋላ ከእስራኤል ቤት ጋር የማደርገው ቃል ኪዳን ይህ ነውና፥ ይላል ጌታ፤ ሕጌን በልቡናቸው አኖራለሁ፥ በልባቸውም እጽፈዋለሁ፤ እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


እኔም ጌታ እንደሆንሁ የሚያውቅ ልብ እሰጣቸዋለሁ፤ በፍጹምም ልባቸው ወደ እኔ ይመለሳሉና፥ ሕዝብ ይሆኑኛል እኔም አምላክ እሆናቸዋለሁ።


ወይስ ሰውነታችሁ፥ ከእግዚአብሔር የተቀበላችሁት፥ በውስጣችሁም የሚኖረው የመንፈስ ቅዱስ ቤተ መቅደስ መሆኑን አታውቁም? እናንተም የራሳችሁ አይደላችሁም።


“እንዲህም ይሆናል፥ በዚያን ቀን እመልሳለሁ ይላል ጌታ፥ ለሰማይ እመልሳለሁ፥ ሰማይም ለምድር ይመልሳል፤


ነገር ግን ኢየሱስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ ክርስቶስን ከሙታን ያስነሣው መንፈስ፥ በውስጣችሁ በሚኖረው በመንፈሱ አማካይነት፥ ለሟች አካላቶቻችሁ ሕይወትን ይሰጠዋል።


ድል የሚነሣ ይህን ይወርሳል፤ አምላክም እሆነዋለሁ፤ እርሱም ልጅ ይሆነኛል።


ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ እንደሆነ የሚመሰክር ሁሉ፥ እግዚአብሔር በእርሱ ይኖራል እርሱም በእግዚአብሔር ይኖራል።


በኢየሩሳሌም ውስጥ እንዲኖሩ አመጣቸዋለሁ፤ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል፥ እኔም በታማኝነትና በጽድቅ አምላክ እሆናቸዋለሁ።


አንድ ሦስተኛውን ክፍል ወደ እሳት አስገባለሁ፤ ብርም እንደሚነጥር አነጥራቸዋለሁ፤ ወርቅም እንደሚፈተን እፈትናቸዋለሁ፤ እነርሱም ስሜን ይጠራሉ፥ እኔም እሰማቸዋለሁ፤ እኔም፦ “ይህ ሕዝቤ ነው” እላለሁ፥ እርሱም፦ “ጌታ አምላኬ ነው” ይላል።


ሥር ሰዳችሁ፥ በፍቅርም ታንጻችሁ ክርስቶስ በልባችሁ በእምነት እንዲኖር፥


ለአባቶቻችሁ በሰጠኋት ምድር ትኖራላችሁ፤ ሕዝብ ትሆኑኛላችሁ እኔም አምላክ እሆናችኋለሁ።


ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል፤ እኔም በእርሱ እኖራለሁ።


ክርስቶስ ግን እንደ ልጅ በቤቱ ላይ የታመነ ነው፥፥ እኛም የምንተማመንበትንና የምንመካበትን ተስፋ አጽንተን ስንይዝ፥ ቤቱ ነን።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ለማቅረብ፥ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ፥ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


በእኛ በሚኖረው በመንፈስ ቅዱስ መልካሙን አደራ ጠብቅ።


እግዚአብሔርን ያየው ማንም የለም፤ እርስ በርሳችን ብንዋደድ እግዚአብሔር በእኛ ይኖራል፥ ፍቅሩም በእኛ ፍጹም ይሆናል።


ደግሞም፥ ‘እናንተ ሕዝቤ አይደላችሁም’ ተብሎ በተነገረላቸው ስፍራ፥ በዚያ ‘የሕያው እግዚአብሔር ልጆች’ ተብለው ይጠራሉ።” ይላል።


አሁንም ዝሙታቸውንና የነገሥታቶቻቸውን ሬሳ ከእኔ ዘንድ ያርቁ፥ እኔም ለዘለዓለም በመካከላቸው እኖራለሁ።


እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። ነገር ግን ማንም የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው፥ እርሱ የክርስቶስ አይደለም።


እንዲህም አለኝ፦ የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ልጆች መካከል ለዘለዓለም የምቀመጥበት የዙፋኔ ስፍራና የእግሬ ጫማ ማሳረፊያ ይህ ነው። የእስራኤል ቤትና ነገሥታቶቻቸው በዝሙታቸውና በከፍታዎቻቸው ባለው በነገሥታቶቻቸው ሬሳ ዳግመኛ ቅዱስ ስሜን አያረክሱም።


በሐዋርያትና በነቢያት መሠረት ላይ ታንጻችኋል፤ የማዕዘኑም ራስ ድንጋይ ክርስቶስ ኢየሱስ ነው፤


በእናንተ ላይ ንጹሕ ውኃ እረጫለሁ እናንተም ትነጻላችሁ፥ ከርኩሰቶቻችሁ ሁሉ ከጣዖቶቻችሁም ሁሉ አነጻችኋለሁ።


“ ‘ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።


የእግዚአብሔር ሰው የሙሴ ጸሎት። አቤቱ፥ አንተ ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ሆንህልን።


ለሌላ አምላክ አትስገዱ፥ ስሙ ቀናተኛ የሆነ ጌታ ቀናተኛ አምላክ ነውና።


“ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይኑሩህ።


“ሁለት ጌቶችን ማገልገል የሚችል ማንም የለም፤ አንዱን ጠልቶ ሌላውን ይወዳል፤ ወይም ወደ አንዱ ይጠጋል ሌላውን ይንቃል፤ ለእግዚአብሔርና ለገንዘብ መገዛት አትችሉም።”


የነገርኳችሁን ነገር ሁሉ ጠብቁ፤ የሌሎችን አማልክት ስም አትጥሩ፥ ከአፍህም አይሰማ።


“በኤፌሶን ወዳለው ቤተ ክርስቲያን መልአክ እንዲህ ብለህ ጻፍ፥ በቀኝ እጁ ሰባቱን ከዋክብት የያዘው በሰባቱም የወርቅ መቅረዞች መካከል የሚመላለሰው እንዲህ ይላል፦


ከጥላውም በታች የሚቀመጡ ይመለሳሉ፤ እንደ አትክልት ስፍራ ይለመልማሉ፤ እንደ ወይንም ተክል ያብባሉ፤ መዓዛቸውም እንደ ሊባኖስ ወይን ጠጅ ይሆናል።


ኤልያስም ወጥቶ ለሰዎቹ፦ “እስከ መቼ ድረስ በሁለት ልብ ስታወላውሉ ትኖራላችሁ? እንግዲህ ጌታ እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱን አምልኩ! ወይም ባዓል እውነተኛ አምላክ ከሆነ እርሱኑ አምልኩ!” አላቸው፤ ሕዝቡ ግን አንዲት ቃል እንኳ አልመለሱም።


በሰገነትም ላይ ለሰማያት ሠራዊት የሚሰግዱትን፥ ለጌታ የሚሰግዱትንና በእርሱም የሚምሉትን፥ በንጉሣቸውም ደግሞ የሚምሉትን፥


በመካከላቸው እንድኖር መቅደስ ይሥሩልኝ።


በዚያን ዘመን፥ ይላል ጌታ፥ ለእስራኤል ወገኖች ሁሉ አምላክ እሆናቸዋለሁ እነርሱም ሕዝብ ይሆኑኛል።


ስምዖን ጴጥሮስም “አንተ ክርስቶስ የሕያው እግዚአብሔር ልጅ ነህ” ብሎ መለሰ።


ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰ፦ “የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል፤ አባቴም ይወደዋል ወደ እርሱም እንመጣለን፤ በእርሱም ዘንድ መኖሪያ እናደርጋለን።


የጌታን ጽዋና የአጋንንትን ጽዋ ልትጠጡ አትችሉም፤ ከጌታ ማዕድና ከአጋንንት ማዕድ ልትካፈሉ አትችሉም።


በእርሱም እናንተ ደግሞ ለእግዚአብሔር መኖሪያ ለመሆን በመንፈስ አብራችሁ ትሠራላችሁ።


ይህ ሳይሆን ቀርቶ ብዘገይ ግን፥ በዚህ በጻፍሁልህ ትእዛዝ የሕያው እግዚአብሔር ቤተ ክርስቲያን፥ የእውነት ዓምድና መሠረት በሆነችው በእግዚአብሔር ማደሪያ ቤት መኖር እንዴት እንደሚገባ እንድታውቅ ነው።


ወይስ “እርሱ በውስጣችን ያሳደረው መንፈስ አብዝቶ ይቀናል” በማለት መጽሐፍ የተናገረው በከንቱ ይመስላችኋልን?


እንዲህ ሲልም በምሳሌ ነገራቸው፦ “የአዲስ ልብስ እራፊን ቀድዶ ባረጀ ልብስ ላይ የሚያኖር ማንም የለም፤ ቢደረግ ግን አዲሱን ይቀደዋል፤ አዲሱም እራፊ ለአሮጌው አይስማማውም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች