Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ቈላስይስ 4:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ዘመኑን እየዋጃችሁ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 በውጭ ካሉት ሰዎች ጋራ ባላችሁ ግንኙነት በጥበብ ተመላለሱ፤ በተገኘውም ዕድል ሁሉ ተጠቀሙ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 በማንኛውም አጋጣሚ ጊዜ እየተጠቀማችሁ በማያምኑት ሰዎች ዘንድ በጥበብ ኑሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ዘመ​ኑን እየ​ዋ​ጃ​ችሁ ከሃ​ይ​ማ​ኖት ወደ ተለዩ ሰዎች በማ​ስ​ተ​ዋል ሂዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ዘመኑን እየዋጃችሁ፥ በውጭ ባሉቱ ዘንድ በጥበብ ተመላለሱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ቈላስይስ 4:5
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በልብ ጥበብን እንድንማር፥ ቀኖቻችንን እንዴት እንደምንቆጥር እንዲህ አስታውቀን።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


እርሱም፥ “ለእናንተ የእግዚአብሔርን መንግሥት ምሥጢር ማወቅ ተሰጥቷአችኋል፤ በውጭ ላሉት ግን ሁሉ ነገር በምሳሌ ይነገራቸዋል፤


መታዘዛችሁ በሁሉም ሰው ዘንድ ደርሶአልና፤ እንግዲህ በእናንተ ደስ ይለኛል፤ ነገር ግን ለመልካም ነገር ጥበበኞች ለክፉ ነገር የዋሆች እንድትሆኑ እፈልጋለሁ።


የክርስቶስ ቃል በሙላት በእናንተ ይኑር፤ በጥበብ ሁሉ እርስ በርሳችሁ ተማማሩ፤ ተመካከሩም፤ በመዝሙርና በውዳሴ በመንፈሳዊም ዝማሬ በልባችሁ በማመስገን ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤


በዚህም በማንም ላይ ሸክም እንዳትሆኑና በውጭ ባሉት ዘንድ በአግባብ እንድትመላለሱ ነው።


በዲያቢሎስ ነቀፋና ወጥመድም እንዳይወድቅ፥ በውጭ ካሉት ሰዎች ደግሞ መልካም ምስክር ሊኖረው ይገባዋል።


ከእናንተ ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፤ ለእርሱም ይሰጠዋል።


ከእናንተ መካከል ጥበበኛና አስተዋይ የሆነ ማን ነው? በመልካም አኗኗር ሥራውን በጥበብ የዋህነት ያሳይ።


ከላይ የሆነችው ጥበብ ግን በመጀመሪያ ንጽሕት ናት፤ ቀጥሎም ሰላም ወዳድ፥ ደግ፥ እሺ ባይ፥ ምሕረትና መልካም ፍሬ የሞላባት፥ ጥርጥርና ግብዝነት የሌለባት ናት።


እንዲሁም እናንተ ሚስቶች ሆይ! ለባሎቻችሁ ታዘዙ፤ በዚህ ዓይነት አንዳንዶች በቃሉ የማያምኑ ቢሆኑም እንኳ ያለ ቃል በሚስቶቻቸው ጠባይ ብቻ ሊሳቡ ይችሉ ይሆናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች