ዘፍጥረት 4:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታም ቃየልን እንዲህ አለው፥ “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፤ “ምንድን ነው ያደረግኸው? የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔርም ቃየልን እንዲህ አለው፤ “ምን አደረግህ? የፈሰሰው የወንድምህ ደም ከምድር ወደ እኔ እየጮኸ ነው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርም አለው፥ “ቃየል! ምን አደረግህ? የወንድምህ የአቤል የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮሃል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኽል። |
‘ትናንትና የናቡቴንና የልጆቹን መገደል አየሁ፤ በዚሁ እርሻ ላይ እንደምቀጣህ እምላለሁ’ የሚል ነበር።” ስለዚህ ኢዩ “እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይፈጸም ዘንድ የኢዮራምን ሬሳ አንሥተህ የናቡቴ ርስት በነበረው እርሻ ላይ በመወርወር ጣለው” ሲል የቅርብ ረዳቱን አዘዘ።
በዚያም ዖዴድ የተባለ የጌታ ነቢይ ነበረ፤ ወደ ሰማርያም የሚመጣውን ጭፍራ ሊገናኘው ወጣ፥ እንዲህም አላቸው፦ “እነሆ፥ የአባቶቻችሁ አምላክ ጌታ ይሁዳን ስለ ተቈጣ በእጃችሁ አሳልፎ ሰጣቸው፥ እናንተም ወደ ሰማይ በሚደርስ ቁጣ ገደላችኋቸው።
ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።
የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የወይን ቦታ የእስራኤል ቤት ነው፤ የይሁዳ ሰዎችም የደስታው አትክልት ናቸው። ፍትሕን ፈለገ፤ ነገር ግን ደም ማፍሰስን አየ፤ ጽድቅን ፈለገ፤ ነገር ግን የጭንቅን ጩኸት ሰማ።
ጴጥሮስም “የጌታን መንፈስ ትፈታተኑ ዘንድ ስለምን ተስማማችሁ? እነሆ፥ ባልሽን የቀበሩት ሰዎች እግር በደጅ ነው፤ አንቺንም ያወጡሻል፤” አላት።
አቤል ከቃየል ይልቅ የሚበልጥን መሥዋዕት ለእግዚአብሔር በእምነት አቀረበ፤ በዚህም እግዚአብሔር ስለ ስጦታው ሲመሰክር፥ እርሱ ጻድቅ እንደሆነ ተመሰከረለት፤ ሞቶም ሳለ በመሥዋዕቱ እስከ አሁን ይናገራል።
ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ ሠራዊቱ መበታተኑን፥ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤