Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




1 ሳሙኤል 13:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ ሠራዊቱ መበታተኑን፥ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፥ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሳሙኤልም፣ “ያደረግኸው ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰ፤ “ሰራዊቱ መበታተኑን፣ አንተም በቀጠርኸው ጊዜ አለመምጣትህን፣ ፍልስጥኤማውያንም በማክማስ መሰብሰባቸውን አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሳሙኤል ግን “ያደረግኸው ነገር ምንድን ነው?” ሲል ጠየቀው። ሳኦልም እንዲህ ሲል መለሰለት፤ “ሕዝቡ ሊከዱኝ ተቃርበው ነበር፤ አንተም በቀጠርከኝ ሰዓት ሳትመጣ ቀረህ፤ ከዚህም በላይ ፍልስጥኤማውያን መጥተው በሚክማስ ተሰለፉ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሳሙ​ኤ​ልም፥ “ያደ​ረ​ግ​ኸው ምን​ድን ነው?” አለ። ሳኦ​ልም፥ “ሕዝቡ ከእኔ ተለ​ይ​ተው እንደ ተበ​ታ​ተኑ፥ አን​ተም በነ​ገ​ር​ኸኝ መሠ​ረት በቀ​ጠ​ሮው ቀን እን​ዳ​ል​መ​ጣህ፥ ፍል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንም ወደ ማኪ​ማስ እንደ ተሰ​በ​ሰቡ አየሁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሳሙኤልም፦ ያደረግኸው ምንድር ነው? አለ። ሳኦልም፦ ሕዝቡ ከእኔ ተለይተው እንደ ተበታተኑ፥ አንተም በቀጠሮው እንዳልመጣህ፥ ፍልስጥኤማውያንም ወደ ማክማስ እንደ ተሰበሰቡ አየሁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




1 ሳሙኤል 13:11
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔርም ሴቲቱን፦ “ይህ ያደረግሽው ምንድነው?” አላት። ሴቲቱም፥ “እባብ አሳተኝና በላሁ” አለች።


ጌታም ቃየልን እንዲህ አለው፥ “ምን አደረግህ? የወንድምህ የደሙ ድምፅ ከምድር ወደ እኔ ይጮኻል።


ከዚያም ኢዮአብ ወደ ንጉሡ ገብቶ እንዲህ አለ፤ “ምንድነው ያደረግከው? እነሆ አበኔር መጥቶልህ፥ በሰላም እንዲሄድ ያሰናበትኸው ለምንድነው?


ወደ ቤት ተመልሶ ገባ፤ ኤልሳዕም “እስከ አሁን የት ነበርክ?” ሲል ጠየቀው። ግያዝም “ጌታዬ፥ ኧረ እኔ የትም አልሄድኩም” ሲል መለሰ።


ወደ ዐያት ይገባሉ፤ በሚግሮን ያልፋሉ፤ ጓዛቸውንም በማክማስ ያከማቻሉ።


ኢያሱም አካንን እንዲህ አለው፦ “ልጄ ሆይ! ለእስራኤል አምላክ ለጌታ ክብር ስጥ፥ ለእርሱም ተናዘዝ፤ ያደረግኸውንም ንገረኝ፤ አትሸሽገኝ።”


ስለዚህ ፍልስጥኤማውያን ወርደው ወደ ጌልገላ ይመጡብኛል፤ እኔም የጌታን ርዳታ አልለመንሁም፥ ብዬ አሰብሁ። ስለዚህ የሚቃጠል መሥዋዕት ማቅረብ ግድ ሆነብኝ።


ሳኦል፥ ልጁ ዮናታንና ሠራዊታቸው በብንያም ግዛት ውስጥ ጌባዕ ተብላ በምትጠራው ስፍራ ነበሩ፤ የፍልስጥኤማውያን ወታደሮች ግን በሚክማስ ሰፍረው ነበር፤


ሳኦል ሦስት ሺህ ሰዎች ከእስራኤል መረጠ፤ ሁለቱ ሺህ በማክማስና በተራራማው አገር በቤቴል ከሳኦል ጋር፥ አንዱ ሺህ ደግሞ በብንያም ግዛት በጊብዓ ከዮናታን ጋር ነበሩ። የቀሩትን ሰዎች ግን ወደ ድንኳኖቻቸው እንዲሄዱ አሰናበተ።


በዚያን ጊዜ አንድ የፍልስጥኤማውያን የጦር ምድብ የሚክማስን መተላለፊያ ለመቆጣጠር ወጣ።


ፍልስጥኤማውያን ሠላሳ ሺህ ሠረገሎች፥ ስድስት ሺህ ፈረሰኞች ቁጥሩ እንደ ባሕር አሸዋ የበዛ ሠራዊት ይዘው እስራኤልን ለመውጋት ተሰበሰቡ፤ ወጥተውም ከቤትአዌን በስተ ምሥራቅ ባለችው በማክማስ ሰፈሩ።


ከድንጋዮቹም አንዱ ከመተላለፊያው በስተ ሰሜን በኩል በሚክማስ ፊት ለፊት የሚገኘው ሲሆን፥ ሁለተኛውም በስተ ደቡብ በኩል በጌባዕ ፊት ለፊት ይገኝ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች