Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ዘፍጥረት 9:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት እና ከሰውም ሁሉ እጅ እሻዋለሁ፥ ከሰው ወንድም እጅ፥ የሰውን ነፍስ እሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ሰውን የገደለ ሁሉ ስለ ሟቹ ደም ተጠያቂ ነው፤ የሟቹን ሰው ደም ከገዳዩ፣ ከእንስሳም ይሁን ከሰው እሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ በተጠያቂነት ላይ እሻዋለሁ፤ ከእንስሶች ሁሉና ከሰውም ላይ እሻዋለሁ፤ ከሰው ሁሉ የሰውን ሕይወት እሻዋለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ነፍ​ሳ​ችሁ ያለ​ች​በ​ትን ደማ​ች​ሁን ከአ​ራ​ዊት ሁሉ እጅ እሻ​ዋ​ለሁ፤ ከሰ​ውም እጅ፥ ከሰው ወን​ድም እጅ፥ የሰ​ውን ነፍስ እሻ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ነፍሳችሁ ያለችበትን ደማችሁን በእርግጥ እሻዋለሁ፥ ከአራዊት ሁሉ እጅ እሻዋለሁ ከስውም እጅ ከስው ወንድም እጅ፤ የስውን ነፍስ እሻለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘፍጥረት 9:5
26 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።


ታዲያ በገዛ ቤቱ፥ በገዛ አልጋው ላይ ዐርፎ የተኛውን ንጹሕ ሰው የገደሉትን ክፉ ሰዎች እንዴት የባሰ ቅጣት አይገባቸውም? ደሙን ከእጃችሁ መፈለግ፥ እናንተን ከምድሪቱ ማጥፋት የለብኝምን?”


እንግዲህ ባለህ ጥበብ፥ ሊፈጸም የሚገባውን ነገር አድርግ፤ ዕድሜ ጠግቦ በሰላም እንዲሞት አትፍቀድለት።


የንጉሥ አካዝያስ እናት ዐታልያ የልጇን መገደል እንደ ሰማች ወዲያውኑ የይሁዳ ንጉሣውያን ቤተሰብ አባላት በሙሉ እንዲገደሉ ትእዛዝ ሰጠች።


እንዲሁም ንጉሡ ኢዮአስ ዮዳሄ ያደረገለትን ቸርነት አላሰበም፥ ልጁንም ዘካርያስን አስገደለው፤ እርሱም ሲሞት፦ “ጌታ ይየው፥ ይበቀለውም” አለ።


ባርያዎቹም አሤሩበት፥ በቤቱም ውስጥ ሳለ ገደሉት።


የአገሩ ሕዝብ ግን በንጉሡ በአሞጽ ላይ ያሤሩበትን ሁሉ ገደሉ፤ የአገሩም ሕዝብ ልጁን ኢዮስያስን በእርሱ ፋንታ አነገሡ።


በጽዮን ለሚኖር ለጌታ ዘምሩ፥ በአሕዛብም መካከል ድንቅ ሥራውን ንገሩ፥


“ሰውን ቢመታ ቢሞትም፥ ፈጽሞ ይሙት።


በሕዝብህ መካከል በሸንጋይነት ወድያና ወዲህ አትመላለስ፤ በባልንጀራህም ሕይወት ላይ መሰነናክል ሆነህ አትቁም፤ እኔ ጌታ ነኝ።


ማናቸውንም ሰው መትቶ የሚገድል ፈጽሞ ይገደል።


እንስሳንም የሚገድል በካሣ ይተካ፤ ሰውን ግን የሚገድል ይገደል።


“ማንኛውም ሰው ሌላውን ሰው በብረት መሣርያ እስኪሞት ድረስ ቢመታው ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል።


ሰውንም ለሞት በሚያበቃው በእጁ ባለው ድንጋይ ቢመታው የተመታውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል።


ሰውንም ለሞት በሚያበቃው በእጁ ባለው በእንጨት መሣርያ ቢመታው የተመታውም ቢሞት፥ እርሱ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ነፍሰ ገዳዩም ፈጽሞ ይገደል።


ወይም በጥላቻ እስኪሞት ድረስ በእጁ ቢመታው፥ የመታው ፈጽሞ ይገደል፤ ነፍሰ ገዳይ ነው፤ ደም ተበቃዩ ባገኘው ጊዜ ነፍሰ ገዳዩን ይግደለው።


በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።


ምናልባትም እየመረመሩ ያገኙት እንደሆነ፥ እግዚአብሔርን ይፈልጉ ዘንድ በምድር ሁሉ ላይ እንዲኖሩ የሰውን ወገኖች ሁሉ ከአንድ ፈጠረ፤ የተወሰኑትንም ዘመኖችና ለሚኖሩበት ስፍራ ዳርቻ መደበላቸው። ቢሆንም ከእያንዳንዳችን የራቀ አይደለም።


“ይሁን እንጂ አንድ ሰው ባልንጀራውን ቢጠላው፥ አድፍጦ ጥቃት ቢያደርስበት፥ ቢገድለውና፥ ከእነዚህ ከተሞች ወደ አንዲቱ ቢሸሽ፥


የሚኖርባት ከተማ ሽማግሌዎች ሰው ልከው ከከተማው ያስመጡት፤ እንዲገድለውም ለደም ተበቃዩ አሳልፈው ይስጡት።


አቤሜሌክ ሰባ ወንድሞቹን በመግደል በአባቱ ላይ ስላደረሰው በደል እግዚአብሔር የእጁን ከፈለው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች