ዘዳግም 15:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፥ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አትጨክንበት፤ ወይም እጅህን አትሰብስብበት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፣ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አታጨክንበት፤ ወይም እጅህን ወደ ኋላ አትሰብስብበት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም “አምላክህ እግዚአብሔር በሚሰጥህ ምድር በምትኖርባቸው ከተሞች ሁሉ አንድ እስራኤላዊ ችግረኛ ሆኖ ቢገኝ የገዛ ወገንህ ስለ ሆነ አትጨክንበት፤ ገንዘብህንም አትንፈገው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ ምድር ካሉ ከተሞች በአንዲትዋ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢቸገር ልብህን አታጽና፤ ለወንድምህ ከመስጠት እጅህን አትመልስ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህ እግዚአብሔር በሰጠህ በአገርህ ደጅ ውስጥ ከሚኖሩ ከወንድሞችህ አንዱ ቢደኸይ፥ ልብህን አታጽና፥ በድሀው ወንድምህ ላይ እጅህን አትጨብጥ። |
‘ዕዳ የሚሠረዝበት ሰባተኛው ዓመት ተቃርቧል’ የሚል ክፉ ሐሳብ አድሮብህ፥ በችግረኛ ወንድምህ ላይ እንዳትጨክንና ምንም ሳትሰጠው እንዳትቀር፥ እርሱም በአንተ ላይ ወደ ጌታ ጮኾ በደለኛ እንዳትሆን ተጠንቀቅ!