Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘዳግም 15:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር፤ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፥ ለድኾችና ለችግረኖች እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 በምድሪቱ ላይ ድኾች ምን ጊዜም አይጠፉም፤ ስለዚህ በዚያ ለሚኖሩ ወንድሞችህ፣ ለችግረኞችና ለድኾች እጅህን እንድትዘረጋ አዝዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 መቼም ቢሆን በምድር ላይ ችግረኛና ድኻ መኖሩ ስለማይቀር በአገርህ ለሚገኙ ድኾችና ችግረኞች ጐረቤቶችህ እጅህን እንድትዘረጋ አዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ድሃ ከም​ድ​ርህ ላይ አይ​ታ​ጣ​ምና ስለ​ዚህ እኔ፦ በሀ​ገ​ርህ ውስጥ ላለው ድሃ፥ ለሚ​ለ​ም​ን​ህም ወን​ድ​ምህ እጅ​ህን ዘርጋ ብዬ አዝ​ዝ​ሃ​ለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ድሆች ከምድሪቱ ላይ አያልቁምና ስለዚህ እኔ፦ በአገርህ ውስጥ ላለው ድሀ ለተቸገረው ወንድምህ እጅህን ትከፍታለህ ብዬ አዝዝሃለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘዳግም 15:11
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ድኾች ምንም ጊዜ ከእናንተ ጋር ናቸው፤ በፈለጋችሁ ጊዜ ልትረዷቸው ትችላላችሁ፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤


ድሆች ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤ እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤


ድሆችስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ይኖራሉና፤እኔ ግን ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር አልኖርም፤” አለ።


ይልቅስ እጅህን ፍታለት፤ የሚያስፈልገውንም ሁሉ አበድረው።


ሀብታምና ድሀ ይገናኛሉ፥ ሁለቱንም የፈጠራቸው ጌታ ነው።


ያላችሁን ሽጡ፤ ምጽዋትም ስጡ፤ ሌባ በማይቀርብበት ብልም በማያጠፋበት በሰማያት የማያልቅ መዝገብ የሚሆኑትን የማያረጁትንም ኮረጆዎች ለራሳችሁ አድርጉ፤


ያላቸውንም ሁሉ አንድነት አደረጉ። መሬታቸውንና ጥሪታቸውንም እየሸጡ፥ ማንኛውም እንደሚፈልግ ለሁሉ ያካፍሉት ነበር።


ለሚጠይቅህ ስጥ፤ ከአንተ ሊበደር ከሚፈልገው ፊትህን አታዙር።


“አምላክህ ጌታ በሚሰጥህ ምድር ላይ ካሉት ከተሞች በአንዲቱ ውስጥ ድኻ ቢኖር፥ በድኻ ወንድምህ ላይ ልብህን አትጨክንበት፤ ወይም እጅህን አትሰብስብበት።


እጅዋን ወደ ድሀ ትዘረጋለች፥ ወደ ችግረኛም እጅዋን ትሰድዳለች።


ማንንም ሰው ባያስጨንቅ፥ ነገር ግን ለባለ ዕዳው መያዣውን ቢመልስ፥ ባይቀማ፥ ከምግቡ ለተራበ ቢሰጥ፥ የተራቆተውንም በልብስ ቢሸፍን፥


በሰባተኛው ዓመት ግን ተዋት አሳርፋትም፤ የሕዝብህ ድሆች ይበሉታል፤ እነርሱ ያስቀሩትንም የሜዳ እንስሳ ይብላው። በወይንህና በወይራህም ላይ እንዲሁ አድርግ።


ለድሀ ቸርነትን የሚያደርግ ለጌታ ያበድራል፥ በጎነቱንም መልሶ ይከፍለዋል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች