2 ተሰሎንቄ 3:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበሉት ትውፊት ሳይሆን ሥራን በመፍታት ከሚኖሩ ወንድሞች ሁሉ እንድትለዩ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድሞች ሆይ፤ ያለ ሥርዐት ከሚመላለስ እና ከእኛ በተቀበላችሁት ትምህርት መሠረት ከማይኖር ወንድም እንድትርቁ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዝዛችኋለን፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድሞች ሆይ! ሥራ ፈት ከሆነውና ከእኛ በተላለፈላችሁ ትውፊት መሠረት ከማይኖር ክርስቲያን ሁሉ እንድትለዩ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድሞች ሆይ! ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዐት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድሞች ሆይ፥ ከእኛ እንደ ተቀበለው ወግ ሳይሆን ያለ ሥርዓት ከሚሄድ ወንድም ሁሉ ትለዩ ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ስም እናዛችኋለን። |
ወንድሞች ሆይ! ከሚለያዩትና እናንተ የተማራችሁትን ትምህርት በመቃወም መሰናክል ከሚያደርጉ ሰዎች እንድትጠነቀቁ አሳስባችኋለሁ፤ ከእነርሱም ራቁ፤
እንግዲህ በቀረውስ ወንድሞች ሆይ! እግዚአብሔርን ለማስደሰት እንዴት መመላለስ እንደሚገባችሁ ከእኛ ዘንድ ተቀብላችኋል፤ በእርግጥም እየተመላለሳችሁ ነው፤ ከዚህም በበለጠ አብዝታችሁ እንድታደርጉት በጌታ በኢየሱስ እንለምናችኋለን፤ እንመክራችኋለንም።
አንዱን ከሌላው በማበላለጥ ምንም ዓይነት ነገር ሳታደርግ፥ ያለ አድልዎ እነዚህን ትዛዛቶች እንድትጠብቅ በእግዚአብሔርና በጌታ በክርስቶስ ኢየሱስ በተመረጡትም መላእክት ፊት አደራ እልሃለሁ።
አእምሮአቸውም በጠፋባቸው እውነትንም በተቀሙ ሰዎች መካከል የማያቋርጥ ጭቅጭቅን ነው፤ እንደነዚህ ያሉት ሰዎች እግዚአብሔርን መምሰል ሀብት ማግኛ ዘዴ መስሎ ይታያቸዋል።