ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው።
2 ነገሥት 5:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ንዕማንም “እንግዲያውስ እባክህ ስድስት ሺህ ብር ልስጥ” ሲል መለሰለት፤ በዚህም አሳቡ በመጽናት ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ቀድመው በፊት በፊቱ እንዲሄዱ አደረገ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ንዕማንም፣ “እባክህ፤ ሁለት መክሊት ውሰድ” በማለት ግያዝን አስጨንቆ ለመነው። ከዚያም ሁለቱን መክሊት ብር፣ በሁለት ከረጢት ውስጥ አስሮ ሁለት ሙሉ ልብስ ጨምሮ ለሁለት አገልጋዮቹ አስያዘ፤ እነርሱም ያን ተሸክመው ከግያዝ ፊት ፊት ሄዱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንዕማንም “እንግዲያውስ እባክህ ስድስት ሺህ ብር ልስጥ” ሲል መለሰለት፤ በዚህም አሳቡ በመጽናት ብሩን በሁለት ከረጢት ሞልቶ ከሁለት መለወጫ ልብሶች ጋር በሁለት አገልጋዮች አስይዞ ከግያዝ ቀድመው በፊት በፊቱ እንዲሄዱ አደረገ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ንዕማንም፥ “ሁለት የብር መክሊት ውሰድ” አለው፤ ሁለቱንም መክሊት ብር ተቀብሎ በሁለት ከረጢት ውስጥ ጨመረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ንዕማንም “ሁለት መክሊት ትወስድ ዘንድ ይፈቀድልህ፤” አለ፤ ግድ አለውም፤ ሁለቱንም መክሊት ብር በሁለት ከረጢት ውስጥ አሰረና ከሁለት መለወጫ ልብስ ጋር ለሁለት ሎሌዎቹ አስያዘ፤ እነርሱም ተሸክመው በፊቱ ሄዱ። |
ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው።
ንጉሥ አክዓብም የሀገሪቱን ሽማግሌዎች ሁሉ ጠርቶ “ይህ ሰው ምን ዓይነት ጠብ እንደሚፈልግ ተመልከቱ። ከዚህ በፊት ሚስቶቼንና ልጆቼን፥ ብሬንና ወርቄን እንዳስረክበው ጠይቆኝ ተስማምቼ ነበር” አላቸው።
እነርሱ ግን እምቢ ለማለት እስኪያሳፍረው ድረስ አጥብቀው ስለ ለመኑት በጉዳዩ ተስማማና ኀምሳ ሰዎች ሄደው ሦስት ቀን ሙሉ ኤልያስን ፈለጉት፤ ነገር ግን ሊያገኙት አልቻሉም፤
ኤልሳዕም “በማገለግለው በሕያው እግዚአብሔር ስም እምላለሁ፤ ምንም ነገር አልቀበልም” ሲል መለሰለት። ንዕማንም ስጦታውን እንዲቀበልለት አጥብቆ ቢለምነውም ኤልሳዕ ሊቀበለው አልፈቀደም፤
ንጉሡም “ይህን ደብዳቤ ይዘህ ወደ እስራኤል ንጉሥ ሂድ” ብሎ ፈቀደለት። ስለዚህም ንዕማን ሠላሳ ሺህ ጥሬ ብር፥ ስድስት ሺህ መሐለቅ ወርቅና ምርጥ የሆነ ዐሥር መለወጫ ልብስ አስጭኖ፥ ጉዞውን ቀጠለ፤
በደቡብ ስላሉ እንስሶች የተነገረ ራእይ። ተባትና እንስት፥ አንበሳ እፉኝትም፥ ተወርዋሪ እባብም በሚወጡባት፥ በመከራና በጭንቀት ምድር በኩል፥ ብልጥግናቸውን በአህዮች ጫንቃ ላይ፥ መዛግብቶቻቸውንም በግመሎች ሻኛ ላይ እየጫኑ ወደማይጠቅሟቸው ሕዝብ ይሄዳሉ።