ዘፍጥረት 33:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ይህንም ያመጣሁልህን ስጦታዬን ተቀበል፥ እግዚአብሔርም በቸርነቱ ጎብኝቶኛልና፥ ለእኔም በቂ አለኝና።” በዚህም መልክ ግድ አለው፥ እርሱም ተቀበለው። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እግዚአብሔር በቸርነቱ አሟልቶ ስለ ሰጠኝ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝና ያቀረብሁልህን ስጦታዬን እባክህ ተቀበለኝ” አለው። ያዕቆብ አጥብቆ ስለ ለመነው፣ ዔሳው እጅ መንሻውን ተቀበለ። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ስለዚህ እባክህ ይህን ያቀረብኩልህን ስጦታ ተቀበለኝ፤ እግዚአብሔር በቸርነቱ የሚያስፈልገኝን ሁሉ ሰጥቶኛል” አለ። ስጦታውን እንዲቀበለው ያዕቆብ ዔሳውን አጥብቆ ለመነው። እርሱም ተቀበለው። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ከወደድኸኝስ ይህችን ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል፤ እግዚአብሔር ራርቶልኛልና፥ ለእኔም ብዙ አለኝና።” እስኪቀበለውም ድረስ ግድ አለው፤ ተቀበለውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ይህችንም ያመጣሁልህን በረከቴን ተቀበል እግዚአብሔር በቸርነት ስጥቶኛልና ለእኔም ብዙ አለኝና። እስኪቀበለውም ድረስ ዘበዘበው። ምዕራፉን ተመልከት |