2 ነገሥት 12:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ብሩን በመቁጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በሣጥኑም ውስጥ ብዙ ገንዘብ መኖሩን በሚያዩበት ጊዜ ሁሉ፣ የንጉሡ ጸሓፊና ሊቀ ካህናቱ መጥተው ወደ እግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የገባውን ገንዘብ ቈጥረው በየከረጢቱ በማስገባት ቋጥረው ያኖሩት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ሣጥኑም በሚሞላበት ጊዜ የቤተ መንግሥቱ ጸሐፊና ሊቀ ካህናቱ እየመጡ ብሩን በመቊጠር በከረጢት እያሰሩ ያኖሩት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 በሣጥኑም ውስጥ የተገኘው ወርቅ ብዙ እንደ ሆነ ባዩ ጊዜ የንጉሡ ጸሓፊና የካህናቱ አለቃ ይመጡ ነበር፤ በእግዚአብሔርም ቤት የተገኘውን ገንዘብ ሁሉ ቈጥረው በከረጢት ውስጥ ያኖሩት ነበር። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ካህኑ ዮዳሄ ግን ሣጥን ወስዶ መክደኛውን ነደለው፤ በመሠዊያውም አጠገብ ወደ እግዚአብሔር ቤት በሚገቡበት መግቢያ በስተ ቀኝ አኖረው፤ ደጁንም የሚጠብቁ ካህናት ወደ እግዚአብሔር ቤት የሚመጣውን ገንዘብ ሁሉ ያኖሩበት ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |