2 ነገሥት 19:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ግን መነሣትህንና መቀመጥህን፥ መውጣትህንና መግባትህን፥ እንዲሁም እኔን መቃወምህን ዐውቃለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም “ ‘እኔ ግን የት እንዳለህ፣ መቼ እንደምትመጣና መቼ እንደምትሄድ፣ በእኔም ላይ እንዴት በቍጣ እንደምትነሣሣ ዐውቃለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ግን መነሣትህንና መቀመጥህን፥ መውጣትህንና መግባትህን፥ እንዲሁም እኔን መቃወምህን ዐውቃለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እኔ ግን መቀመጫህንና መውጫህን መግቢያህንም፥ በእኔም ላይ የተቈጣኸውን ቍጣ ዐውቄአለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እኔ ግን መቀመጫህንና መውጫህንም መግቢያህንም፥ በእኔም ላይ የተቈጠኸውን ቍጣ አውቄአለሁ። |
ስለዚህም አኪሽ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “አንተ ለእኔ ታማኝ ስለ መሆንህ በሕያው ጌታ እምላለሁ፤ ወደዚህም ጦርነት ዘምተህ ብትዋጋ ደስ ባለኝ ነበር፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እኔን ማሳዘን የሚችል በደል ሠርተህ አላገኘሁህም፤ ግን ሌሎቹ ገዢዎች የአንተን አብሮ መዝመት አልፈቀዱም።