Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 121 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)


1 የዕርገት መዝሙር።

1 የዕርገት መዝሙር። ዐይኖቼን ወደ ተራሮቹ አነሣሁ፥ ረዳቴ ከወዴት ይምጣ?

2 ረዳቴ ሰማይና ምድርን ከሠራ ከጌታ ዘንድ ነው።

3 እግርህ እንዲናወጥ አይፈቅድም፥ የሚጠብቅህም አይተኛም።

4 እነሆ፥ የእስራኤል ጠባቂ አይተኛም አያንቀላፋምም።

5 ጌታ ጠባቂህ ነው፥ ጌታ በቀኝ እጅህ በኩል ይጋርድሃል።

6 ፀሐይ በቀን አይመታህም፥ ጨረቃም በሌሊት እንዲሁ።

7 ጌታ ከክፉ ሁሉ ይጠብቅሃል፥ ነፍስህንም ይጠብቃታል።

8 ከዛሬ ጀምሮ እስከ ዘለዓለም ጌታ መውጣትህንና መግባትህን ይጠብቃል።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች