1 ሳሙኤል 29:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)6 ስለዚህም አኪሽ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “አንተ ለእኔ ታማኝ ስለ መሆንህ በሕያው ጌታ እምላለሁ፤ ወደዚህም ጦርነት ዘምተህ ብትዋጋ ደስ ባለኝ ነበር፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እኔን ማሳዘን የሚችል በደል ሠርተህ አላገኘሁህም፤ ግን ሌሎቹ ገዢዎች የአንተን አብሮ መዝመት አልፈቀዱም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም6 ስለዚህ አንኩስ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “ሕያው እግዚአብሔርን አንተ ታማኝ ነህ፤ ወደ እኔ እዚህ ከመጣህበት ቀን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ምንም ጥፋት ያላገኘሁብህ ስለ ሆነ፣ ዐብረኸኝ ብትዘምት በበኩሌ ደስተኛ ነበርሁ፤ ነገር ግን ገዦቹ አልተቀበሉህም፤ ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም6 ስለዚህም አኪሽ ዳዊትን ጠርቶ እንዲህ አለው፤ “አንተ ለእኔ ታማኝ ስለ መሆንህ በሕያው አምላክ ስም እምላለሁ፤ ወደዚህም ጦርነት ዘምተህ ብትዋጋ ደስ ባለኝ ነበር፤ ወደ እኔ ከመጣህበት ጊዜ ጀምሮ እኔን ማሳዘን የሚችል በደል ሠርተህ አላገኘሁህም፤ ነገር ግን ሌሎቹ ገዢዎች የአንተን አብሮ መዝመት አልፈቀዱም፤ ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)6 አንኩስም ዳዊትን ጠርቶ፥ “ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ በፊቴ ጻድቅና ደግ ነህ፤ ከእኔም ጋር በጭፍራው በኩል መውጣትህና መግባትህ በፊቴ መልካም ነው፤ ወደ እኔ ከመጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አንዳች ክፋት አላገኘሁብህም፤ ነገር ግን በአለቆች ዘንድ አልተወደድህም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)6 አንኩስም ዳዊትን ጠርቶ፦ ሕያው እግዚአብሔርን! አንተ ቅን ነህ፥ ከእኔም ጋር በጭፍራው በኩል መውጣትህና መግባትህ በፊቴ መልካም ነው፥ ወደ እኔም ከመጣህ ጀምሮ እስከ ዛሬ ድረስ አንዳች ክፋት አላገኘሁብህም፥ ነገር ግን በአለቆች ዘንድ አልተወደድህም። ምዕራፉን ተመልከት |