1 ሳሙኤል 25:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሳሙኤልም ሞተ፤ መላው እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ ራማ ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤል ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ አርማቴም ባለው ቤቱም ቀበሩት። ከዚያም ዳዊት ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሳሙኤል ሞተ፤ መላው እስራኤላውያንም በአንድነት መጥተው አለቀሱለት፤ ከዚያም በኋላ በራማ በሚገኘው መኖሪያ ቤቱ ቀበሩት። ከዚያም በኋላ ዳዊት ወደ ፋራን ምድረ በዳ ሄደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሳሙኤልም ሞተ፤ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፤ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ማዖን ምድረ በዳ ወረደ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሳሙኤልም ሞተ፥ እስራኤልም ሁሉ ተሰብስበው አለቀሱለት፥ በአርማቴምም በቤቱ ቀበሩት። ዳዊትም ተነሥቶ ወደ ፋራን ምድረ በዳ ወረደ። |
በዚያች ምድር የሚኖሩ የከነዓን ሰዎችም በአጣድ አውድማ የሆነውን ልቅሶ ባዩ ጊዜ፦ “ይህ ለግብጽ ሰዎች ታላቅ ልቅሶ ነው አሉ፥” ስለዚህም የዚያን ቦታ ስም አቤል ምጽራይም ብለው ጠሩት፥ እርሱም በዮርዳኖስ ማዶ ነው።
ተጉዘውም በፋራን ምድረ በዳ በቃዴስ ወዳሉት ወደ ሙሴና ወደ አሮን ወደ እስራኤልም ልጆች ማኅበር ሁሉ መጡ፤ ወሬውንም ለእነርሱና ለማኅበሩ ሁሉ ነገሩአቸው፥ የምድሪቱንም ፍሬ አሳዩአቸው።
በዚህ ጊዜ ሳሙኤል ሞቶ ነበር፤ እስራኤላውያንም ሁሉ በገዛ ከተማው በራማ አልቅሰው ቀበሩት። ሳኦልም ሙታን ሳቢዎችንና መናፍስት ጠሪዎችን ከምድሪቱ አባሯቸው ነበር።