1 ሳሙኤል 14:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሰፈር በእርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሰፈር በዕርሻ ላይና በሕዝብ ሁሉ መካከል ሽብር ሆነ፤ ከተማ ጠባቂዎችና አደጋ ጣዮችም ሁሉ ተንቀጠቀጡ፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ሽብሩም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተላከ ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በገጠር የነበሩ ፍልስጥኤማውያንም ሁሉ ተሸበሩ፤ አደጋ ጣዮችና በሰፈር የነበሩ ወታደሮችም ሁሉ በፍርሃት ተንቀጠቀጡ፤ እግዚአብሔር በላከባቸውም አስጨናቂ ሽብር መሬት ተንቀጠቀጠች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሰፈሩና በእርሻውም ድንጋጤ ሆነ፤ በሰፈሩ የተቀመጡ ሕዝብና የሚዋጉትም ሁሉ ተሸበሩ፤ መዋጋትም አልቻሉም፤ ምድሪቱም ተናወጠች፤ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ድንጋጤ መጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሰፈሩም በእርሻውና በሕዝቡም ሁሉ መካከል ሽብር ነበረ፥ በሰፈሩ የተቀመጡና ለምርኮ የወጡት ተሸበሩ፥ ምድሪቱም ተናወጠች፥ ከእግዚአብሔርም ዘንድ ታላቅ ሽብር ሆነ። |
በሾላው ዛፎች ጫፍ ላይ የሰልፍ ድምፅ ስትሰማም፥ ጌታ የፍልስጥኤማውያንን ሠራዊት ለመምታት ቀድሞህ ወጥቶአል ማለት ነውና በዚያን ጊዜ ፍጠን።”
ሰዎቹንም እንዲህ አለቻቸው፦ “ጌታ ምድሪቱን እንደ ሰጣችሁ፥ ከእናንተም የተነሣ በፍርሃት መዋጣችንን፥ በምድሪቱም የሚኖሩት ሁሉ ከፊታችሁ በፍርሃት እንደ ቀለጡ አወቅሁ።
ሳሙኤል የሚቃጠለውን መሥዋዕት በሚያሳርግበት ጊዜ፥ ፍልስጥኤማውያን እስራኤልን ለመውጋት ቀረቡ። ጌታ ግን በዚያ ዕለት በፍልስጥኤማውያን ላይ ከባድ የነጐድጓድ ድምፅ አንጐዳጐደባቸው፤ እነርሱም እጅግ ተሸበሩ፤ በእስራኤላውያን ፊት ድል ተመተውም ሸሹ።