ዘፍጥረት 35:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ተነሥተውም ሄዱ፥ የእግዚአብሔርም ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፥ የያዕቆብንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ያንም ቦታ ለቅቀው ሄዱ፤ እግዚአብሔርም በዙሪያቸው በነበሩት ከተሞች ሁሉ ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስለ ለቀቀባቸው የያዕቆብን ልጆች ያሳደዳቸው አልነበረም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ያዕቆብና ልጆቹ ያንን ስፍራ ትተው ለመሄድ ተነሡ፤ እግዚአብሔር በዙሪያቸው በነበሩት ሰዎች ላይ ፍርሀትና ድንጋጤ ስላሳደረባቸው ሊያሳድዱአቸው አልደፈሩም። ምዕራፉን ተመልከትየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 እስራኤልም ከሴቄም ሄደ፤ እግዚአብሔርንም መፍራት በዙሪያቸው ባሉት ከተሞች ሁሉ ወደቀ፤ የእስራኤልንም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 የእግዚአብሔር ፍርሃት በዙሪያቸው ባሉች ከተሞች ሁሉ ወደቀ የያዕቆብም ልጆች ለማሳደድ አልተከተሉአቸውም። ምዕራፉን ተመልከት |