የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

ማስታወቂያዎች


መላው መጽሐፍ ቅዱስ ብሉይ ኪዳን አዲስ ኪዳን




መዝሙር 68:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐ​መፅ የሚ​ከ​ብ​ቡኝ ጠላ​ቶቼ በረቱ፤ ያል​ወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ይከ​ፈ​ሉ​ኛል።

ምዕራፉን ተመልከት

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም ተቀኙ፤ በደመናት ላይ የሚሄደውን ከፍ አድርጉት፤ ስሙ እግዚአብሔር በተባለው ፊት፣ እጅግ ደስ ይበላችሁ።

ምዕራፉን ተመልከት

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጻድቃንም ደስ ይበላቸው፥ በእግዚአብሔርም ፊት ሐሤት ያድርጉ፥ በደስታም እልል ይበሉ።

ምዕራፉን ተመልከት

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ ለስሙም የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፤ በደመናዎች ላይ ለሚጓዘው መንገድ አዘጋጁ፤ ስሙ እግዚአብሔር ነው፤ በፊቱ ደስ ይበላችሁ!

ምዕራፉን ተመልከት



መዝሙር 68:4
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በቅ​ዱስ ስሙም ትከ​ብ​ራ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም አባ​ረ​ሩኝ፤ ከበ​ቡ​ኝም፤ ዐይ​ና​ቸ​ው​ንም ወደ ምድር ዝቅ ዝቅ አደ​ረጉ።


ከወ​ር​ቅና ከክ​ቡር ዕንቍ ይልቅ ይወ​ደ​ዳል፤ ከማ​ርና ከማር ወለ​ላም ይልቅ ይጣ​ፍ​ጣል።


አንተ ጻድ​ቁን ትባ​ር​ከ​ዋ​ለ​ህና፤ አቤቱ፥ እንደ አላ​ባሽ ጋሻ ከለ​ል​ኸን።


መን​ገ​ድ​ህን በም​ድር፥ በአ​ሕ​ዛ​ብም ሁሉ ዘንድ ማዳ​ን​ህን እና​ውቅ ዘንድ፥


ለአ​ሕ​ዛብ በቅን ትፈ​ር​ድ​ላ​ቸ​ዋ​ለ​ህና፥ አሕ​ዛ​ብ​ንም በም​ድር ላይ ትመ​ራ​ለ​ህና


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አመ​ስ​ግኑ፤ ለስ​ሙም ዘምሩ፤ ወደ ምዕ​ራብ ለወ​ጣው መን​ገ​ድን አብጁ፤ ስሙ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፥ በፊ​ቱም ደስ ይበ​ላ​ችሁ፤ ከፊ​ቱም የተ​ነሣ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለሙሴ ነገ​ረው፤ እን​ዲህ ሲል፥ “ያለና የሚ​ኖር እኔ ነኝ፤ እን​ዲህ ለእ​ስ​ራ​ኤል ‘ያለና የሚ​ኖር’ ወደ እና​ንተ ላከኝ ትላ​ቸ​ዋ​ለህ” አለው።


ለአ​ብ​ር​ሃ​ምም፥ ለይ​ስ​ሐ​ቅም፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም ሁሉን እን​ደ​ሚ​ችል አም​ላክ ተገ​ለ​ጥሁ፤ ነገር ግን ስሜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አል​ታ​ወ​ቀ​ላ​ቸ​ውም ነበር።


ለአ​ብ​ር​ሃ​ምና ለይ​ስ​ሐቅ፥ ለያ​ዕ​ቆ​ብም እሰ​ጣት ዘንድ እጄን ወደ ዘረ​ጋ​ሁ​ባት ምድር አገ​ባ​ች​ኋ​ለሁ፤ እር​ስ​ዋ​ንም ርስት አድ​ርጌ እሰ​ጣ​ች​ኋ​ለሁ፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ።”


ደስታ ከጻድቃን ጋር ትኖራለች፤ የኃጥኣን ተስፋ ግን ትጠፋለች።


ስለ ግብፅ የተ​ነ​ገረ ራእይ። እነሆ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፈ​ጣን ደመና ተቀ​ምጦ ወደ ግብፅ ይመ​ጣል፤ የግ​ብ​ፅም የእ​ጆ​ቻ​ቸው ሥራ​ዎች በፊቱ ይዋ​ረ​ዳሉ፤ የግ​ብ​ፃ​ው​ያ​ንም ልብ በው​ስ​ጣ​ቸው ይቀ​ል​ጣል።


የዐ​ዋጅ ነጋሪ ቃል በም​ድረ በዳ፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን መን​ገድ ጥረጉ፤ ለአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም ጎዳና በበ​ረሃ አስ​ተ​ካ​ክሉ።


ሂዱና በበሬ ውስጥ ግቡ፤ ለሕ​ዝ​ቤም መን​ገ​ድን ጥረጉ፤ ድን​ጋ​ዮ​ቹ​ንም ከጎ​ዳ​ናው አስ​ወ​ግዱ፤ ለአ​ሕ​ዛ​ብም አላማ ያዙ።


እንደ ፍቁሩ አም​ላክ ማንም የለም፤ በሰ​ማይ የሚ​ኖ​ረው፥ በጠ​ፈ​ርም በታ​ላ​ቅ​ነት ያለው እርሱ ረዳ​ትህ ነው።