Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -

መዝሙር 68 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)


ለመ​ዘ​ም​ራን አለቃ በመ​ለ​ከ​ቶች የዳ​ዊት መዝ​ሙር

1 አቤቱ፥ ውኃ እስከ ነፍሴ ደር​ሶ​ብ​ኛ​ልና አድ​ነኝ።

2 በጥ​ልቅ ረግ​ረግ ጠለ​ቅሁ ኀይ​ልም የለ​ኝም፤ ወደ ጥልቁ ባሕ​ርም ደረ​ስሁ ማዕ​በ​ሉም አሰ​ጠ​መኝ።

3 በጩ​ኸት ደከ​ምሁ፥ ጉሮ​ሮ​ዬም ሻከረ፤ አም​ላ​ኬን ተስፋ ሳደ​ርግ ዐይ​ኖቼ ፈዘዙ።

4 በከ​ንቱ የሚ​ጠ​ሉኝ ከራሴ ጠጉር በዙ፤ በዐ​መፅ የሚ​ከ​ብ​ቡኝ ጠላ​ቶቼ በረቱ፤ ያል​ወ​ሰ​ድ​ሁ​ትን ይከ​ፈ​ሉ​ኛል።

5 አቤቱ፥ አንተ ስን​ፍ​ና​ዬን ታው​ቃ​ለህ፥ ኃጢ​አ​ቴም ከአ​ንተ አል​ተ​ሰ​ወ​ረም።

6 አቤቱ፥ የሠ​ራ​ዊት አም​ላክ፥ የሚ​ሹህ በእኔ አይ​ፈሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ ሆይ፥ ተስፋ የሚ​ያ​ደ​ር​ጉህ በእኔ አይ​ነ​ወሩ።

7 ስለ አንተ ስድ​ብን ታግ​ሻ​ለ​ሁና፥ እፍ​ረ​ትም ፊቴን ሸፍ​ኖ​ኛ​ልና።

8 ለወ​ን​ድ​ሞቼ እንደ ባዕድ፥ ለአ​ባ​ቴና ለእ​ና​ቴም ልጆች እንደ እን​ግዳ ሆን​ሁ​ባ​ቸው።

9 የቤ​ትህ ቅን​ዓት በል​ቶ​ኛ​ልና፥ የሚ​ሰ​ድ​ቡ​ህም ስድብ በላዬ ወድ​ቆ​አ​ልና።

10 ሰው​ነ​ቴን በጾም አደ​ከ​ም​ኋት፥ ስድ​ብ​ንም ሆነ​ብኝ።

11 ማቅ ለበ​ስሁ መተ​ረ​ቻም ሆን​ሁ​ላ​ቸው።

12 በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤ ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ።

13 እኔስ በጸ​ሎቴ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይቅ​ር​ታው በጊ​ዜው ነው፤ ይቅ​ር​ታህ ብዙ ሲሆን መድ​ኃ​ኒቴ ሆይ፥ በእ​ው​ነት አድ​ነኝ።

14 እን​ዳ​ይ​ው​ጠኝ ከረ​ግ​ረግ አው​ጣኝ፤ ከጠ​ላ​ቶ​ችና ከጥ​ልቅ ውኃ አስ​ጥ​ለኝ።

15 የውኃ ማዕ​በል አያ​ስ​ጥ​መኝ፥ ጥል​ቁም አይ​ዋ​ጠኝ፥ ጕድ​ጓ​ዶ​ችም አፋ​ቸ​ውን በኔ ላይ አይ​ክ​ፈቱ፤

16 አቤቱ፥ ምሕ​ረ​ትህ መል​ካም ናትና ስማኝ፤ እንደ ይቅ​ር​ታ​ህም ብዛት ወደ እኔ ተመ​ል​ከት፤

17 ከባ​ሪ​ያ​ህም ፊት​ህን አት​መ​ልስ፤ ተጨ​ን​ቄ​አ​ለ​ሁና ፈጥ​ነህ ስማኝ።

18 ነፍ​ሴን ተመ​ል​ክ​ተህ ተቤ​ዣት፤ ስለ ጠላ​ቶ​ችም አድ​ነኝ።

19 አንተ ስድ​ቤን፥ እፍ​ረ​ቴ​ንም፥ ነው​ሬ​ንም ታው​ቃ​ለህ፤ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁኝ ሁሉ ፊት።

20 ሰው​ነቴ ስድ​ብ​ንና ውር​ደ​ትን ታገ​ሠች፤ አዝኜ ተቀ​መ​ጥሁ፥ የሚ​ያ​ጽ​ና​ና​ኝ​ም አጣሁ።

21 በመ​ብሌ ውስጥ ሐሞ​ትን ጨመሩ፥ ለጥ​ማ​ቴም ሆም​ጣ​ጤን አጠ​ጡኝ።

22 ማዕ​ዳ​ቸው በፊ​ታ​ቸው ለወ​ጥ​መድ፥ ለፍ​ዳና ለዕ​ን​ቅ​ፋት ትሁ​ን​ባ​ቸው፤

23 ዐይ​ኖ​ቻ​ቸው እን​ዳ​ያዩ ይጨ​ልሙ፥ ጀር​ባ​ቸ​ውም ዘወ​ትር ይጉ​በጥ።

24 መዓ​ት​ህን በላ​ያ​ቸው አፍ​ስስ፥ የቍ​ጣህ መቅ​ሠ​ፍ​ትም ያግ​ኛ​ቸው።

25 ከተ​ማ​ቸው በረሃ ትሁን፥ በድ​ን​ኳ​ኖ​ቻ​ቸ​ውም የሚ​ቀ​መጥ አይ​ገኝ፤

26 አንተ የቀ​ሠ​ፍ​ኸ​ውን እነ​ርሱ ተከ​ት​ለ​ዋ​ልና፥ በቍ​ስ​ሌም ላይ ቍስ​ልን ጨመ​ሩ​ብኝ።

27 በኀ​ጢ​አ​ታ​ቸው ላይ ኃጢ​አ​ትን ጨም​ር​ባ​ቸው፥ በጽ​ድ​ቅ​ህም አይ​ግቡ።

28 ከሕ​ያ​ዋን መጽ​ሐፍ ይደ​ም​ሰሱ፥ ከጻ​ድ​ቃ​ንም ጋር አይ​ጻፉ።

29 እኔ ድሃና ቍስ​ለኛ ነኝ፤ የፊቴ፥ መድ​ኀ​ኒት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተቀ​በ​ለኝ።

30 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ስም በዝ​ማሬ አመ​ሰ​ግ​ና​ለሁ፥ በም​ስ​ጋ​ናም ከፍ ከፍ አደ​ር​ገ​ዋ​ለሁ።

31 ቀን​ድና ጥፍር ካላ​በ​ቀለ ከእ​ም​ቦሳ ይልቅ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ደስ አሰ​ኘ​ዋ​ለሁ።

32 ድሆች ይዩ ደስም ይበ​ላ​ቸው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፈል​ጉት፥ ነፍ​ሳ​ች​ሁም ትድ​ና​ለች።

33 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ድሆ​ችን ሰም​ቶ​እ​ቸ​ዋ​ልና፥ እስ​ረ​ኞ​ች​ንም አል​ና​ቃ​ቸ​ው​ምና።

34 ሰማ​ይና ምድር፥ ባሕ​ርም፥ በእ​ር​ስ​ዋም የሚ​ን​ቀ​ሳ​ቀሱ ሁሉ ያመ​ሰ​ግ​ኑ​ታል።

35 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጽዮ​ንን አድ​ኗ​ታ​ልና፥ የይ​ሁ​ዳም ከተ​ሞች ይሠ​ራ​ሉና፤ በዚ​ያም ይቀ​መ​ጣሉ ይወ​ር​ሷ​ታ​ልም።

36 የባ​ሪ​ያ​ዎ​ችህ ዘሮች ይኖ​ሩ​ባ​ታል፥ ስም​ህን የሚ​ወ​ድዱ በው​ስጧ ይቀ​መ​ጣሉ።

ተከተሉን:



ማስታወቂያዎች