መጽሐፈ ጦቢት 13:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቤተ መቅደሱ በውስጥሽ በደስታ እንዲሠራ፥ ለጌታ የሚገባውን ምስጋና አቅርቢለት፥ የዘመናትንም ንጉሥ ባርኪ፤ በውስጥሽ ያሉትን ስደተኞች እንዲያጽናና፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ያዘኑትን ሁሉ በመጭው ትውልድ ዘመን ሁሉ እንዲያፈቅራቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በበጎ ሥራ ለእግዚአብሔር ተገዢ፤ ባንቺም ዘንድ ድንኳኑ በደስታ እንድትሠራ የዘለዓለሙን ንጉሥ አመስግኚ፤ በዚያም ያሉ የተማረኩ ሰዎች ደስ ይላቸዋል። በዘለዓለማዊ ትውልድም ሁሉ የተጠሉ በአንቺ ምክንያት ይወደዳሉ። |