ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ጦቢት 13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)ጽዮን 1 ጦቢትም እንዲህ አለ፦ “ለዘለዓለም የሚኖር እግዚአብሔር ይባረክ፥ መንግሥቱ በዘመናት ሁሉ ይኖራልና። 2 የሚቀጣም፥ የሚምርም እርሱ ነውና። እርሱ ወደ ሲኦል ጥልቀት ያወርዳል፥ ከጥልቅ ጥፋትም ያወጣል፥ ከእጁ የሚያመልጥ ማንም የለም፤ 3 የእስራኤል ልጆች ሆይ በመንግሥታት መካከል ምስጋናውን አውጁ፥ በመካከላቸው በትኖአችኋልና፤ 4 እዚያም ትልቅነቱን አሳይቷችኋል፥ በሕያዋን ሁሉ ፊት አሞግሱት፤ እርሱ ጌታችን ነው፥ እርሱ አምላካችን ነው፤ እርሱ አባታችን ነው፥ እርሱ ለዘለዓለም አምላክ ነው። 5 በኃጢአታችሁ ምክንያት ቢቀጣችሁም፥ በሁላችሁም ላይ ምሕረትን ያደርጋል፤ ተበታትናችሁ ከምትገኙባቸው አገሮች ሁሉ መካከል ይሰበስባችኋል። 6 በፊቱ እውነትን የሆነውን ለማድረግ በሙሉ ልባችሁና በሙሉ ንፍሳችሁ ወደ እርሱ ከተመለሳችሁ፥ እርሱም ወደ እናንተ ይመለሳል፥ ፊቱንም ከዚህ በኋላ አይሰውርም። ያደረገላችሁን አስቡ፥ ድምፃችሁንም ከፍ አድርጋችሁ ምስጋናን ስጡት፤ የጽድቅ ጌታ ባርኩት፤ የዘመናትንም ንጉሥ አሞግሱት። እኔ ተማርኬ በመጣሁበት አገር ሆኜ፥ ምስጋናውን እዘምራለሁ፤ ኃጢአት በሠራች ከተማ ላይ ኃይሉንና ትልቅነቱን አስታውቃለሁ። ኃጢአተኞች ወደ እርሱ ተመለሱ፥ ስራችሁ በፊቱ ትክክለኛ ይሁን፥ ምናልባት ምሕረት ያደርግላችሁ፥ ይራራላችሁ ይሆናል።” 7 እኔ አምላኬን አሞግሰዋለሁ፥ ነፍሴም በሰማዩ ንጉሥ ትደሰታለች። 8 ትልቅነቱ በሁሉም በምላስ ላይ ይሁን፤ ምስጋናውም በኢየሩሳሌም ይዘምር። 9 ቅድስቲቱ ከተማ ኢየሩሳሌም ሆይ፥ በሠራሽው ሥራ ምክንያት እግዚአብሔር ይቀጣሻል፤ ነገር ግን ለጻድቅ ልጆች አሁንም ይራራላቸዋል። 10 ቤተ መቅደሱ በውስጥሽ በደስታ እንዲሠራ፥ ለጌታ የሚገባውን ምስጋና አቅርቢለት፥ የዘመናትንም ንጉሥ ባርኪ፤ በውስጥሽ ያሉትን ስደተኞች እንዲያጽናና፥ በአንቺ ውስጥ ያሉ ያዘኑትን ሁሉ በመጭው ትውልድ ዘመን ሁሉ እንዲያፈቅራቸው። 11 በምድር ሁሉ ላይ ደማቅ ብርሃን ያበራል፥ ለሰማዩ ንጉሥ በእጆቻቸው ሥጦታ ይዘው፥ ከሁሉም የምድር ዳርቻዎች፥ ብዙ መንግሥታት ከሩቅ ወደተቀደሰው ስምህ ይመጣሉ፥ ከትውልድ ወደ ትውልድ ደስታቸውን ያውጃሉ፥ የተመረጠችውም ስም ለመጪው ትውልድ ይኖራል። 12 የሚያዋርዱሽ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ፥ የሚያጠፉሽ ሁሉ፥ ግንቦችሽን የሚያፈርሱ ሁሉ፥ ህንፃዎችሽን የሚያወድሙ፥ ቤቶችሽን የሚያቃጥሉ ሁሉ የተረገሙ ይሁኑ። መልሶ የሚገነባሽ ግን ለዘለዓለም የተባረኩ ይሁኑ። 13 በዚያን ጊዜ በጻድቁ ልጆች ምክንያት ትፈነድቂያለሽ፥ ትደሰቻለሽም፤ እነርሱ ሁሉ ተሰብስበው የዘመናትን ጌታ ይባርካሉና። 14 አንቺን የሚወዱ ሁሉ የተባረኩ ናቸው፥ በሰላምሽ የሚደሰቱ የተባረኩ ናቸው፥ በደረሰብሽ ቅጣት ሁሉ ስለ አንቺ የሚያዘኑ የተባረኩ ናቸው፤ እነርሱ በመጪዎቹ ቀኖች መባረክሽን አይተው በውስጥሽ ሆነው ይደሰታሉና። 15 ነፍሴ ሆይ ታላቁን ንጉሥ፥ ጌታን ባርኪ፤ 16 ምክንያቱም ኢየሩሳሌም ለዘለዓለም ቤቱ ሆና እንደ አዲስ ትታነጻለችና፥ የአንቺን ክብር ለማየትና፥ የሰማዩን ንጉሥ ለማመሰገን፥ ከቤተሰቦቼ አንዱ እንኳ ቢቀር፥ ምንኛ ደስታ ነበር፤ የኢየሩሳሌም በሮች ከሰንፔርና ከኤመራልድ ይሠራሉ፥ ግንቦችሽም ከውድ ዐለቶች ይፈለፈላሉ፥ የኢየሩሳሌም ህንፃዎች ከወርቅ፥ ቅጥሮቻቸውም ከንጹህ ወርቅ ይሠራሉ፤ 17 የኢየሩሳሌም መንገዶች በቀያይ የከበሩ ድንጋዮችና በዖፌር ድንጋዮች ይሸፈናሉ። 18 የኢየሩሳሌም በሮች የምስጋና መዝሙርን ያስተጋባሉ፥ ቤቶችም በሙሉ “ሃሌ ሉያ! የእስራኤል አምላክ ይባረክ” ይላሉ። በውስጥሽም ቅዱሱን ስም፥ ለዘለዓለም ዓለም ይባርካሉ። |