ስትሄድም ይመሩሃል፥ ስትተኛ ይጠብቁሃል፥ ስትነሣ ያነጋግሩሃል።
በምትሄድበት ሁሉ ይመሩሃል፤ በምትተኛበት ጊዜ ይጠብቁሃል፤ በምትነቃበት ጊዜም ያነጋግሩሃል።
እነርሱም በጒዞህ ይመሩሃል፤ ስትተኛም ይጠብቁሃል፤ ስትነቃም ያነጋግሩሃል።
ስትሄድም ይመራሃል፤ ከአንተም ጋር ይኖር ዘንድ ውሰደው። ስትተኛ ይጠብቅሃል፤ ስትነሣም ያነጋግርሃል።
አንተን እንዳልበድል፥ ቃልህን በልቤ ሰወርሁ።
ቃልህን አስብ ዘንድ ዐይኖቼ ለመማለድ ቀደሙ።
ሕግህም ተድላዬ ነው፥ ደንቦችህም አማካሪዎቼ ናቸው።
በእንግድነቴ አገር ሥርዓትህ መዝሙር ሆነችኝ።
ጎልማሳ መንገዱን በምን ያነጻል? ቃልህን በመጠበቅ ነው።
አቤቱ፥ ሕግህን እንደምን እጅግ ወደድሁ! ቀኑን ሁሉ እርሱ ትዝታዬ ነው።
የሰውን ሥራ አፌ እንዳይናገር ፈቃዴ ነው፥ ስለ ከንፈሮችህ ቃል ጭንቅ የሆኑ መንገዶችን ጠበቅሁ።
እኔ ተኛሁ አንቀላፋሁም፥ ጌታም ደግፎኛልና ነቃሁ።
ብርሃንህንና እውነትህን ላክ፥ እነርሱ ይምሩኝ፥ ወደ ቅድስናህ ተራራና ወደ ማደሪያህ ይውሰዱኝ።
ማመዛዘን ይጠብቅሃል፥ ማስተዋልም ይከላከልልሃል፥