ምሳሌ 22:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ላይ ይገኛሉ፥ ነፍሱን ግን የሚጠብቅ ከእነርሱ ይርቃል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በክፉዎች መንገድ ላይ እሾኽና ወጥመድ አለ፤ ራሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ይርቃል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እሾህና ወጥመድ በጠማማ ሰው መንገድ ናቸው፤ ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነርሱ ያመልጣል። |
ጌታ አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድና አሽክላ፥ ለጎናችሁም መቅሠፍት፥ ለዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ ጌታ አምላካችሁ ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንደማያሳድዳቸው ፈጽማችሁ እወቁ።