Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 23:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታ አምላካችሁ ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ ወጥመድና አሽክላ፥ ለጎናችሁም መቅሠፍት፥ ለዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ ጌታ አምላካችሁ ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንደማያሳድዳቸው ፈጽማችሁ እወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከእንግዲህ ከፊታችሁ እንደማያወጣቸው ይህን ልታውቁ ይገባል፤ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስም ወጥመድና እንቅፋት፣ ለጀርባችሁ ጅራፍ፣ ለዐይኖቻችሁም እሾኽ ይሆኑባችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 አምላካችሁ እግዚአብሔር እነዚህን ሕዝቦች ከፊታችሁ ማባረሩን እንደማይቀጥል በእርግጥ ዕወቁ፤ እንዲያውም አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች መልካም ምድር እስክትጠፉ ድረስ እነዚህን ሕዝቦች ለጀርባችሁ መግረፊያ፥ ለዐይኖቻችሁ እንደሚወጋ እሾኽ፥ እንዲሁም አደገኛ ወጥመድና መውደቂያ ጒድጓድ ይሆኑባችኋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከሰ​ጣ​ችሁ ከዚ​ህች ከመ​ል​ካ​ሚቱ ምድር እስ​ክ​ት​ጠፉ ድረስ መው​ደ​ቂ​ያና ወጥ​መድ፥ በእ​ግ​ራ​ች​ሁም ችን​ካር፥ በዐ​ይ​ና​ች​ሁም እሾህ ይሆ​ኑ​ባ​ች​ኋል እንጂ አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲያ እነ​ዚ​ህን አሕ​ዛብ ከፊ​ታ​ችሁ እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው ራሳ​ችሁ ዕወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 አምላካችሁ እግዚአብሔር ከሰጣችሁ ከዚህች ከመልካሚቱ ምድር እስክትጠፉ ድረስ መውደቂያና ወጥመድ፥ በጎናችሁም መግረፊያ፥ በዓይናችሁም እሾህ ይሆኑባችኋል እንጂ አምላካችሁ እግዚአብሔር ከእንግዲህ ወዲያ እነዚህን አሕዛብ ከፊታችሁ እንዳያሳድዳቸው ፈጽማችሁ እወቁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 23:13
24 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ጌታ እግዚአብሔርም በእጅህ አሳልፎ የሚጥላቸውን ሕዝቦች ሁሉ ታጠፋቸዋለህ፥ ዓይንህም አታዝንላቸውም፤ ወጥመድ ይሆንብሃልና አማልክቶቻቸውን አታምልካቸው።


የአገሩንም ሰዎች ከፊታችሁ ባታሳድዱ፥ ያስቀራችኋቸው ለዓይናችሁ እንደ ስንጥር ለጎናችሁም እንደ እሾህ ይሆኑባችኋል፥ በምትቀመጡባትም ምድር ያስጨንቁአችኋል።


በምድርህ አይቀመጡ አማልክቶቻቸውን በማገልገል እኔን እንድትበድል ያደርጉሃልና፥ ይህም ለአንተ ወጥመድ ይሆንብሃል።”


በሰይፍ ስለትም ይወድቃሉ፤ ወደ አሕዛብ ሁሉ ይሰደዳሉ፤ የአሕዛብም ዘመን እስኪፈጸም ድረስ ኢየሩሳሌም በአሕዛብ የተረገጠች ትሆናለች።


ለመብሌ ሐሞት ሰጡኝ፥ ለጥማቴም ሆምጣጤ አጠጡኝ።


እንዲሁም ፈቃዱን ለመፈጸም ታስረው ከተያዙበት ከዲያብሎስ ወጥመድ ወጥተው ወደ ልቦናቸው እንዲመለሱ ያደርጋቸዋልና።


ከዚህም የተነሣ ባቢሎናውያንን ስለ ፈሩ እስራኤላውያን ሀብታሞችም ድኾችም ከጦር ሠራዊት መኰንኖች ጋር በአንድነት ተነሥተው ወደ ግብጽ ሸሹ።


ፈጽመህ እንደምትጠፋ እኔ ዛሬ እነግርሃለሁ፤ ዮርዳኖስን ተሻግረህ እንድትወርሳትም በምትገባባት ምድር ረጅም ዘመን አትኖርም።


በቁጣና በመቅሠፍት፥ በታላቅም መዓት ጌታ ከምድራቸው ነቀላቸው፤ ወደ ሌላም ምድር ጣላቸው። ዛሬም በዚያው ይገኛሉ።’


ትወርሱአት ዘንድ ዮርዳኖስን ተሻግራችሁ ከምትገቡባት ምድር ፈጥናችሁ እንደምትጠፉ እኔ ዛሬ ሰማይንና ምድርን በእናንተ ላይ ለምስክርነት እጠራለሁ፥ ፈጽሞም ትጠፋላችሁ እንጂ ረጅም ዘመን አትኖሩባትም።


ንጉሡም በዚያ እነርሱን አስደብድቦ በማሠቃየት በሞት ቀጣቸው። በዚህም ዓይነት የይሁዳ ሕዝብ ከአገራቸው ተማርከው ተወሰዱ።


በተለይም በዕድሜ እየሸመገለ በሄደ መጠን ለባዕዳን አማልክት እንዲሰግድ አደረጉት፤ ሰሎሞን እግዚአብሔርን በታማኝነት በማገልገል እንደ አባቱ እንደ ዳዊት ሆኖ አልተገኘም።


የፈርዖንም አገልጋዮች፦ “ይህ ሰው እስከ መቼ ወጥመድ ይሆንብናል? ጌታ አምላካቸውን እንዲያገለግሉት ወንዶቹን ልቀቃቸው፥ ግብጽስ እንደ ጠፋች ገና አላወቅህምን?” አሉት።


በመካከልህ ወጥመድ እንዳይሆኑብህ አንተ በምትገባባት ምድር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ቃል ኪዳን እንዳታደርግ ተጠንቀቅ፤


ሴቶች ልጆቻቸውን ለወንድ ልጆችህ ብትወስድ፥ ሴቶች ልጆቻቸው አምላኮቻቸውን ተከትለው ሲያመነዝሩ ልጆችህን ከአምላኮቻቸው ጋር እንዲያመነዝሩ ያደርጓቸዋል።


ከእንግዲህም ወዲያ ለእስራኤል ቤት የሚወጋ እሾህ፥ በዙሪያቸውም ካሉ ከናቋቸው ሁሉ የሚያቆስል ኩርንችት አይሆንም፤ እኔም ጌታ እግዚአብሔር እንደሆንሁ ያውቃሉ።


ኢያሱ በሞተ ጊዜ ከተዋቸው በምድሪቱ ከነበሩት ሕዝቦች አንዳቸውንም በፊታቸው አሳድጄ አላስወጣም።


እግዚአብሔርም በእስራኤል ላይ ተቆጥቶ የይሁዳን መንግሥት ብቻ በመተው እስራኤላውያንን ከፊቱ አስወገደ።


እግዚአብሔር እስራኤላውያንን ሁሉ ተዋቸው፤ ከፊቱም እስኪወገዱ ድረስ በዝባዦች ለሆኑት ጠላቶቻቸው አሳልፎ በመስጠት ቀጣቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች