ኤርምያስ 5:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወፍ እንደሞላበት የወፍ ቀፎ፥ እንዲሁ ቤቶቻቸው በሽንገላ ተሞልቶአል፤ ስለዚህም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወፎች እንደ ሞሉት ጐጆ፣ ቤታቸው በማጭበርበር የተሞላ ነው፤ ባለጠጎችና ኀያላን ሆነዋል፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አዳኝ ወፎችን ይዞ በወፎች ጎጆ እንደሚያሰፍር፥ እነርሱም ቤታቸውን ከብዝበዛ ባገኙት ሀብት ይሞላሉ፤ ብርቱዎችና ሀብታሞች የሆኑትም ስለዚህ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፤ በዚህም ከብረዋል ባለጸጎችም ሆነዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀፎ ወፎችን እንደሚሞላ፥ እንዲሁ ቤታቸው ሽንገላን ሞልታለች፥ እንዲሁም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል። |
ጌታ ከአለቆችና ከሕዝቡ ሽማግሌዎች ጋር እንዲህ ሲል ይፋረዳል፤ “የወይኔን ቦታ ያጠፋችሁ እናንተ ናችሁ፤ ከድኾች የዘረፋችሁትም በቤታችሁ ይገኛል፤
አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?
በብርቱም ድምፅ “ታላቂቱ ባቢሎን ወደቀች! ወደቀች! የአጋንንትም ማደሪያ ሆነች፤ የርኩሳንም መናፍስት ሁሉ መጠጊያ የርኩሳንና የተጠሉም ወፎች ሁሉ መጠጊያ ሆነች፤