ኢሳይያስ 1:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሬ ጌታውን፤ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሬ ጌታውን፣ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሬ ባለቤቱን ያውቃል፤ አህያም የጌታውን ጋጥ ያውቃል፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ምንም አያውቅም፤ ሕዝቤም አያስተውልም።” የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሬ ገዢውን አህያም የጌታውን ጋጥ ዐወቀ፤ እስራኤል ግን አላወቁኝም፤ ሕዝቤም አላስተዋሉኝም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሬ የገዢውን አህያም የጌታውን ጋጣ አወቀ፥ እስራኤል ግን አላወቀም፥ ሕዝቤም አላስተዋለም። |
ጫፎችዋ በደረቁ ጊዜ ይሰበራሉ፥ ሴቶችም መጥተው ያቃጥሉአቸዋል፤ የማያስተውል ሕዝብ ነውና ፈጣሪው አይራራለትም፤ ሠሪውም ምሕረት አያደርግለትም።
በግብዣቸው ላይ በገናና መሰንቆ፤ ከበሮና ዋሽንት እንዲሁም የወይን ጠጅ አለ፤ ነገር ግን ለጌታ ሥራ ቦታ አልሰጡም፤ ለእጆቹም ሥራ ክብር አላሳዩም።
መብል የሚወዱ ከቶ የማይጠግቡ ውሾች ናቸው፤ እረኞቹም ማስተዋል የማይችሉ ናቸው፤ ሁሉም ወደ መንገዳቸው ዞሩ፥ ከፊተኛው እስከ ኋለኛው ድረስ ሁሉ፥ እያንዳንዳቸው ወደ ጥቅማቸው ዘወር ብለዋል።
ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።
“ሕዝቤ ሰንፈዋልና አላወቁኝም፤ ሰነፎች ልጆች ናቸው፥ ማስተዋልም የላቸውም፤ ክፉ ነገርን ለማድረግ ብልሃተኞች ናቸው፥ በጎ ነገርን ማድረግ ግን አያውቁም።”
ሕዝቤ የጠፉ በጎች ሆነዋል፤ እረኞቻቸው አሳቱአቸው፥ ከተራሮችም ላይ እንዲያፈገፍጉ አደረጉአቸው፤ ከተራራ ወደ ኮረብታ ሄደዋል፥ በረታቸውንም ረስተዋል።