Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሆሴዕ 2:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ስለዚህ፥ እነሆ፥ መንገድሽን በእሾህ እዘጋለሁ፤ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን እቀጥርባታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እርሷም እህል፣ ዘይትና አዲስ የወይን ጠጅ የሰጠኋት፣ ለበኣል አምልኮ ያደረጉትን፣ ብርንና ወርቅን ያበዛሁላት፣ እኔ እንደ ሆንሁ አላወቀችም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እርስዋ እህልን፥ የወይን ጠጅን፥ የወይራ ዘይትን የሰጠኋት፥ እኔ እንደ ሆንኩ ከቶ አልተገነዘበችም፤ እኔ ያበዛሁላትን ብርና ወርቅ “በዓል” ተብሎ ለሚጠራው ጣዖት አቀረበች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 እር​ስ​ዋም እህ​ል​ንና ወይ​ንን ዘይ​ት​ንም የሰ​ጠ​ኋት፥ ብር​ንና ወር​ቅን ያበ​ዛ​ሁ​ላት እኔ እንደ ሆንሁ አላ​ወ​ቀ​ችም። እር​ስዋ ግን ወር​ቁ​ንና ብሩን ለጣ​ዖት አደ​ረ​ገች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስለዚህ፥ እነሆ፥ መንገድሽን በእሾህ እዘጋለሁ፥ መንገድዋንም እንዳታገኝ ቅጥርን እቀጥርባታለሁ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሆሴዕ 2:8
27 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሬ ጌታውን፤ አህያ የባለቤቱን ጋጥ ያውቃል፤ እስራኤል ግን አላወቀም፤ ሕዝቤም አላስተዋለም።”


አሁንም ኃጢአትን እጅግ አብዝተው ይሠራሉ፤ በብራቸውም ለራሳቸው ቀልጦ የተሠራ ምስልን፥ እንደ ጥበባቸውም ጣዖታትን ሠርተዋል፤ ሁሉም የሞያተኞች ሥራ ናቸው። ስለ እነርሱም የሚሠዉ ሰዎች፦ “እምቦሳውን ይሳሙ” ይላሉ።


ለራሳቸው ነገሥታትን አነገሡ፥ ከእኔም ዘንድ አይደለም፤ አለቆችንም ሾሙ፥ እኔም አላወቅሁም፤ ለመጥፊያቸው ከብራቸውና ከወርቃቸው ጣዖታትን ለራሳቸው ሠሩ።


ዝሙት ተከትለዋልና፤ ወይንና አዲስ ወይን ጠጅ ልብን አጥፍቶአልና።


እግዚአብሔርን ለማወቅ ስላልፈለጉ እግዚአብሔር ተገቢ ያልሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ለማይረባ አእምሮ አሳልፎ ሰጣቸው፤


ከጥቂት ቀንም በኋላ ታናሹ ልጅ ገንዘቡን ሁሉ ሰብስቦ ወደ ሩቅ አገር ሄደ፤ ከዚያም እያባከነ ገንዘቡን በተነ።


ስለዚህ ለመረቡ ይሠዋል፥ ለአሽክላውም ያጥናል። በእነርሱ ድርሻው ሰብቷልና፥ መብሉም በዝቶአልና።


አለበለዚያ ዕራቁትዋን እንድትሆን እገፍፋታለሁ፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር አደርጋታለሁ፥ በጥምም እገድላታለሁ።


እኔን ለማስቆጣት፥ ለሰማይ ንግሥት እንጐቻ እንዲያደርጉ፥ ልጆች እንጨት ይሰበስባሉ፥ አባቶችም እሳት ያነድዳሉ፥ ሴቶችም ዱቄት ይለውሳሉ፤ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥ ቁርባን ያፈስሳሉ።


ወርቁን ከኮሮጆ የሚያፈስሱ፥ ብሩንም በሚዛን የሚመዝኑ እነርሱ አንጥረኛውን ይቀጥራሉ፤ እርሱም አምላክ አድርጎ ይሠራዋል፤ ለዚያም ይጐነበሱለታል ይሰግዱለትማል።


ወደ ዕርሻ ወጥተው ወይናቸውን ለቅመው ከጨመቁ በኋላ በአምላካቸው ቤት የደስታ በዓል አደረጉ፤ በዚያም እየበሉና እየጠጡ አቤሜሌክን ሰደቡ።


እስራኤል ፍሬውን የሚሰጥ የተትረፈረፈ ወይን ነው፤ እንደ ፍሬው ብዛት መሠዊያዎችን አብዝቶአል፤ እንደ ምድሩም ብልጥግና መጠን ሐውልቶችን እያሳመሩ ሠርተዋል።


ባለጸጋ እንድትሆን ኃይልና ብርታት የሰጠህ ጌታ አምላክህ መሆኑን አስታውስ፤ ይህም ዛሬ እንደሚያደርገው ሁሉ ከቀድሞ አባቶችህ ጋር በመሐላ የገባውን ቃል ኪዳን ያጸና ዘንድ ነው።


ክብር ባለው አልጋ ላይ ተቀመጥሽ፥ በፊት ለፊቱም ማዕድ ተዘጋጅቶ ነበር፥ ዕጣኔንና ዘይቴንም በዚያ ላይ አስቀመጥሽ።


ኤፍሬም በተናገረ ጊዜ ፍርሃት ነበረ፥ በእስራኤልም መካከል ታበየ፤ ነገር ግን በኣልን በማምለክ በበደለ ጊዜ ሞተ።


አቤቱ አምላካችን ሆይ! ለቅዱስ ስምህ ቤት እንድንሠራ ይህ ያዘጋጀነው ባለጠግነት ሁሉ ከእጅህ የመጣ ነው፥ ሁሉም የአንተ ነው።


እንዳላልፍ መንገዴን ዘግቶታል፥ በጎዳናዬም ጨለማ አኑሮበታል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች