Este libro no es inspirado por Dios y no forma parte del canon cristiano ni del Tanaj judío. Se muestra solo con fines históricos y de estudio. Ver explicación completa መጽሐፈ ጥበብ 1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)ትክክለኛ ፍርድን ስለ መሻት 1 የምድር ገዥዎች ሆይ፥ ጽድቅን ውደዷት፥ የእግዚአብሔርንም ኀይል በበጎ ዕውቀት አስቡት፥ በቅን ልቡናም ፈልጉት። 2 በማይፈታተኑት ሰዎች ዘንድ እርሱ ይገኛልና። በማይክዱት ሰዎችም ዘንድ ይገለጣልና። 3 ጠማማ አሳብ ከእግዚአብሔር ያርቃል፤ የተፈተነችም ኀይል አላዋቂዎችን ትዘልፋቸዋለች። 4 በተተነኰለች ሰውነት ጥበብ አትገባምና፤ ለኀጢአት በተገዛ ሰውነትም አታድርምና። 5 ተግሣጽን የሚገልጽ መንፈስ ቅዱስ ክፉውን ትምህርት ያርቃልና፥ ከሰነፎችም ልቡና ድል ነሥቶ ይሄዳልና በሚመጣም ጊዜ ክፉውን ይዘልፈዋል። 6 ጥበብን የሚገልጽ መንፈስ ሰው ወዳጅ ነውና፥ በከንፈሩ የሚሳደበውንም አያነጻውም። እግዚአብሔር በኵላሊቶቹ ምስክር ነውና፥ ነዋሪ ጕበኛም ልቡናውን ይመረምረዋል፤ አንደበቱንም ይሰማዋል። 7 የእግዚአብሔር መንፈስ ዓለሙን መልትዋልና። ዓለምንም ሁሉ የያዘው እርሱ ነገራቸውን ፈጽሞ ያውቃልና። 8 ስለዚህ ከሚነገር ከዐመፃ ነገራቸው ምንም ከእርሱ አይሰወርም። ሥራውን በመግለጥ ፍርዱ አይተላለፈውምና። 9 ክፉዎችን በልቡናቸው ምክር ይመረምራቸዋልና፥ የነገራቸውም ድምፅ ለበደላቸው ዘለፋ ሊሆንባቸው ወደ እግዚአብሔር ይደርሳልና። 10 ስለ ቅንአት ሥራውን ሁሉ የሚሰማ አይደለምና፥ የነጐርጓርም ድምፅ ከእርሱ አይሰወርም። 11 ከማይረባ ነጐርጓር ተጠበቁ፤ ከሐሜትም አንደበታችሁን ከልክሉ፤ በስውር የሚሆን ነገር በከንቱ አይወጣምና፥ የሚወጋና የሚዋሽ አፍ ሰውን ይገድላልና። እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረም 12 በሕይወታችሁ ስሕተት ለሞት አትቅኑ፤ በእጃችሁም ሥራ ጥፋትን አታምጡ። 13 እግዚአብሔር ሞትን አልፈጠረምና፤ የሕያዋንም ጥፋት ደስ አያሰኘውምና። 14 ነዋሪ ይሆን ዘንድ ፍጥረቱን ፈጥሮአልና፥ የዓለም መፈጠርም ለድኅነት ነውና፥ በእነርሱም ዘንድ የጥፋት መርዝ አልነበረምና፥ ለሲኦልም በምድር ላይ ግዛት አልነበረውምና። 15 ጽድቅ አትሞትምና። 16 ክፉዎች ግን በእጃቸውና በቃላቸው ጠሩት፥ ባልንጀራም አስመሰሉት። በእርሱም ጠፉ። 17 የእርሱ ወገን መሆን ይገባቸዋልና ከእርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረጉ። |