Biblia Todo Logo
La Biblia Online
- Anuncios -




ሕዝቅኤል 47:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

3 ሰው​ዮ​ውም የመ​ለ​ኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥ​ራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ቍር​ጭ​ም​ጭ​ሚት ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

3 ያም ሰው የመለኪያውን ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ በመሄድ፣ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ ከዚያም እስከ ቍርጭምጭሚት በሚደርሰው ውሃ ውስጥ መራኝ፤

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

3 ሰውዬው ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ፥ አንድ ሺህ ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ቁርጫምጭሚት ድረስ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

3 ያም ሰው በያዘው የመለኪያ ገመድ ወደ ምሥራቅ የሚፈሰውን ውሃ በመከተል አንድ ሺህ ክንድ ለካ፤ በዚያም ውሃ እየተራመድኩ እንድሻገር አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ቊርጭምጭሚቴ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

3 ሰውዬውም ገመዱን በእጁ ይዞ ወደ ምሥራቅ ወጣ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፥ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃም እስከ ቍርጫምጭሚት ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 47:3
12 Referencias Cruzadas  

ወደ​ዚ​ያም አመ​ጣኝ፤ እነ​ሆም መልኩ እን​ደ​ሚ​ያ​ን​ፀ​ባ​ርቅ ናስ መልክ የመ​ሰለ አንድ ሰው በዚያ ነበረ፤ በእ​ጁም የተ​ልባ እግር ገመ​ድና የመ​ለ​ኪያ ዘንግ ነበረ፤ እር​ሱም በበሩ አጠ​ገብ ቆሞ ነበር።


በሰ​ሜ​ኑም በር በኩል አወ​ጣኝ፤ በስተ ውጭ በአ​ለው መን​ገድ፥ ወደ ምሥ​ራቅ ወደ​ሚ​መ​ለ​ከት በስተ ውጭ ወዳ​ለው በር አዞ​ረኝ፤ እነ​ሆም ውኃው በቀኝ በኩል ይፈ​ስስ ነበር።


ደግሞ አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ጉል​በት ደረሰ፤ ደግ​ሞም አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ወገብ ደረሰ።


ዓይኖቼንም አነሣሁ፣ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በውስጥዋም ክብርን እሆናለሁ፥ ይላል እግዚአብሔር።


እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”


አሁን ግን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ከፍ ከፍ ብሎና የመ​ን​ፈስ ቅዱ​ስን ተስፋ ከአብ ገን​ዘብ አድ​ርጎ ይህን ዛሬ የም​ታ​ዩ​ት​ንና የም​ት​ሰ​ሙ​ትን አፈ​ሰ​ሰው።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


በትር የሚመስል መለኪያ ለእኔ ተሰጠኝ፤ እንዲህም ተባልሁ “ተነሥተህ የእግዚአብሔርን መቅደስና መሠዊያውን በዚያም የሚሰግዱትን ለካ።


የተናገረኝም ከተማይቱንና ደጆችዋን ቅጥርዋንም ይለካ ዘንድ የወርቅ ዘንግ ነበረው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos