Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 47:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ጉል​በት ደረሰ፤ ደግ​ሞም አንድ ሺህ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ወገብ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ቀጥሎም አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ጕልበት ወደሚደርስም ውሃ መራኝ፤ ከዚያም ሌላ አንድ ሺሕ ክንድ ለካ፤ እስከ ወገብ ወደሚደርስም ውሃ መራኝ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንደገና አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ጉልበት ድረስ ነበር። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሳለፈኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ድረስ ነበር።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እንደገናም አንድ ሺህ ክንድ ለካና እንድራመድ አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ጒልበቴ ደረሰ፤ ቀጥሎም አንድ ሺህ ክንድ ለክቶ በውሃው ውስጥ እንድራመድ አደረገኝ፤ ውሃውም እስከ ወገቤ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ደግሞ አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ጕልበት ደረሰ። ደግሞም አንድ ሺህ ለካ በውኃውም ውስጥ አሻገረኝ፥ ውኃውም እስከ ወገብ ደረሰ።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 47:4
5 Referencias Cruzadas  

ሰው​ዮ​ውም የመ​ለ​ኪያ ገመድ በእጁ ይዞ ወደ ምሥ​ራቅ ወጣ፤ አንድ ሺህም ክንድ ለካ፤ በው​ኃ​ውም ውስጥ አሻ​ገ​ረኝ፤ ውኃ​ውም እስከ ቍር​ጭ​ም​ጭ​ሚት ደረሰ።


ደግሞ አንድ ሺህ ለካ ልሻ​ገ​ረ​ውም የማ​ል​ች​ለው ወንዝ ሆነ፤ ውኃ​ውም ጥልቅ ነበረ፤ የሚ​ዋ​ኝ​በ​ትም ውኃ ነበረ፤ ሰው ሊሻ​ገ​ረው የማ​ይ​ች​ለው ወንዝ ነበረ።


በኀ​ይ​ልና በተ​አ​ም​ራት፥ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ ኀይ​ልና ድንቅ ሥራን በመ​ሥ​ራ​ትም፥ ከኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም አው​ራ​ጃ​ዎች ጀምሬ እስከ እል​ዋ​ሪ​ቆን ድረስ እንደ አስ​ተ​ማ​ርሁ፥ የክ​ር​ስ​ቶ​ስ​ንም ወን​ጌል ፈጽሞ እንደ ሰበ​ክሁ እና​ገር ዘንድ እደ​ፍ​ራ​ለሁ።


ይህም ወደ እና​ንተ የደ​ረ​ሰ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ጸጋ በእ​ው​ነት ከሰ​ማ​ች​ሁ​በ​ትና ከአ​ያ​ች​ሁ​በት ቀን ጀምሮ በመ​ላው ዓለም ያድ​ግና ያፈራ ዘንድ ነው።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios


¡Síguenos en WhatsApp! Síguenos